በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ሚሳዬል ምርቶች ላይ ማዕቀብ እንዲጠል ጠየቀች


የፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚቢግናዉ ራዬና የዩክሬን አቻቸው ዲሚትሮ ኩሌባ
የፖላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዚቢግናዉ ራዬና የዩክሬን አቻቸው ዲሚትሮ ኩሌባ

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ሚሳዬል ኢንደስቱሪ ላይ ማዕቀብ እንዲጥል ዛሬ ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት ጠየቁ፡፡

“የሩሲያ የሚሳዬል ምርቶች ሊቆሙ ይገባል” ያሉት ኩሌባ፣ በአውሮፓ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ላይ ይህንኑ መልዕክታቸውን ከህብረቱ የውጭ ፖሊሲ ሊቀመንበር ጆሴፍ ቦሬል ጋር የተነጋገሩበት መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ለዩክሬን ለሚሰጠው የመከላከያ እርዳታም ኩሌባ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ሩሲያ ሚሳዬሎችዋን የዩክሬንን ከተሞች በመደብደብ በአገሪቱ ቁልፍ የሆኑ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ የመሳሰሉትን የመሰረተ ልማቶችን እንደምትደበድብ ተገልጿል፡፡

በሌላም በኩል የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደርሌይን ሩሲያ በዩክሬን ላይ በፈጸመችው ወንጀል የምትከሰስበት ልዩ ፍርድ ቤት እንዲቋቋም ትናንት በሰጡት መግለጫ መጠየቃቸው ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG