በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ አራት የዩክሬን ግዛቶችን የመቀላቀል ህዝብ ውሳኔ ዛሬ ይጠናቀቃል

አራት የዩክሬን ግዛቶችን ወደግዛቷ ለመቀላልቀል ሩሲያ የመደበቻቸው ባለሥልጣናት የሚያካሂዱትና የዩክሬን መንግሥትና ምዕራባውያን የይስሙላ ነው ሲሉ የተቃወሙት የውሳኔ ህዝብ ዛሬ ማክሰኞ ይጠናቀቃል፡፡ 

የዋይት ሀውስ ቃል አቀባይ ከሪን ዣን ፒዬር ትናንት ለሪፖተሮች በሰጡት መግለጫ “ውጤቱን አስመልክቶ ሩሲያ ይፋ የምታደርገውን የትኛውንም የሀሰት መግለጫ በመላው ዓለም ካሉ አጋሮቻችን ጋር በመሆን ውድቅ እንዳደርገዋለን” ብለዋል፡፡

ቃል አቀባይዋ አይይዘውም “አሁን እየተመለከትነው ያለውን በኃይል የመቀላቀል ድርጊት የሚቀጥል ከሆነ ምላሹን ለመስጠት በኛ በኩል የምናደርገው ከአጋሮቻችንና ተባባሪዎቻችን ጋር በመሆን በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ የሚፈጥርና ከባድ ዋጋ የሚያስከፍል ተጨማሪ ጫና ለማድረግ ተዘጋጅተናል” ብለዋል፡፡ “ለዚህም አቋማችንን ግልጽ አድርገናል” ሲሉም ቃል አቀባይዋ አክለዋል፡፡

ሩሲያ በምትቆጣጠራቸው የሉሃንስክ ከኻርሰን ግዛቶችና በኃይል በተያዙት የዶኔትስክና ዛፕሮዢዥያ ግዝቶች የህዝብ ውሳኔው ድምጽ መሰጠት የተጀመረው ባላፈው ዓርብ መሆኑም ተነገሯል፡፡

XS
SM
MD
LG