በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እህል የጫነ መርከብ ከዩክሬን ወጣ


ጋዜጠኛው “ራዞኒ” ተብሎ የሚጠራውና የሲየራሊዮንን ባንዲራ የሚያውለበልበው መርከብ 26 ሺህ 527 ቶን ወይም ከ265 ሺህ በላይ ኲንታል በቆሎ ጭኖ ከዩክሬን ኦዴሳ ወደብ ሲነሳ እየተመለከተ እአአ ነሃሴ 1/2022
ጋዜጠኛው “ራዞኒ” ተብሎ የሚጠራውና የሲየራሊዮንን ባንዲራ የሚያውለበልበው መርከብ 26 ሺህ 527 ቶን ወይም ከ265 ሺህ በላይ ኲንታል በቆሎ ጭኖ ከዩክሬን ኦዴሳ ወደብ ሲነሳ እየተመለከተ እአአ ነሃሴ 1/2022

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች ወዲህ እህል የጫነ የመጀመሪያ መርከብ ነገ ኢስታንቡል - ቱርክ እንደሚደርስ ይጠበቃል።

መርከቡ የነጫነው እህል በቀጥታ ወደ ወደብ ከመግባቱ በፊት ምርመራ እንደሚደረግ የቱርክ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።

“ራዞኒ” ተብሎ የሚጠራውና የሲየራሊዮንን ባንዲራ የሚያውለበልበው መርከብ 26 ሺህ 527 ቶን ወይም ከ265 ሺህ በላይ ኲንታል በቆሎ ጭኖ ከዩክሬን ኦዴሳ ወደብ የለቀቀው ትናንት፤ ሰኞ ማለዳ እንደነበረ ታውቋል።

ባለፈው ዓመት የተመረተ 20 ቢሊዮን ቶን ወይም ከ200 ቢሊዮን ኲንታል በላይ እህል በሃገሪቱ ወደቦች ላይ ተከማችቶ ወደ ሌሎች ሃገሮች ለመላክ በመጠባበቅ ላይ መሆኑን የዩክሬን የግብርና ባለሥልጣናት ተናግረዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዜሌንስኪ በትናንት ዕለታዊ የቪዲዮ መልዕክታቸው ላይ የእህሉ መላክ “እየጨመረ የመጣውን የዓለም የምግብ ቀውስ ለማስቆም የመጀመሪያው አዎንታዊ እርምጃ ነው” ብለዋል።

ቱርክና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከዩክሬን እህል እንዲወጣ ለማስቻል ከሩሲያ ጋር መስማማታቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG