በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዜሌንስኪ ሩሲያ ሊሲቻንስክ’ን መቆጣጠሯን ተከትሎ የተያዙባቸውን አካባቢዎች መልሰው እንደሚቆጣጠሩ ተናገሩ


ዩክሬን ውስጥ በሊሲቻንስክ፣ ሉሃንስክ ክልል፣ የአካባቢው ነዋሪ በጥቃቱ በተጎዳ ሕንፃ ፊት ለፊት ሲራመድ
ዩክሬን ውስጥ በሊሲቻንስክ፣ ሉሃንስክ ክልል፣ የአካባቢው ነዋሪ በጥቃቱ በተጎዳ ሕንፃ ፊት ለፊት ሲራመድ

የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜሌነስኪ ኃይሎቻቸው በምስራቃዊ ዩክሬን በቁጥጥራቸው ሥር ከነበሩት አካባቢዎች የመጨረሻዋ የሆነችውን ሊሲቻንስክ’ን ለቀው ከወጡ በኋላ በዘመናዊ መሳሪያዎች በመታገዝ የተነጠቁ ግዛቶቻቸውን እንደሚያስመልሱ ተናገሩ፡፡

ዜሌነስኪ ዘወትር በየምሽቱ በሚያደርጉት መሰረት ትናንት እሁድ ሰሙት ለሕዝባቸው ከሚያሰሙት ንግራቸው አንዱ በሆነው ባሰሙት ንግግራቸው ሩሲያ ጠንካራ ኃይሏን በምስራቃዊ ዩክሬን በሚገኘው የዶናባስ ክልል ማሰማራቷን እና የዩክሬን ኃይሎች በበኩላቸው ከዩናይትድ ስቴትስ ባገኟቸውን “ዩ ሃይ” በመባል የሚታወቁትን ተንቀሳቃሽ የሮኬት ማስወንጨፊያ መሳሪያዎች እና ሌሎች ከምዕራብ አጋሮችቸው ባገኟቸው የረጅም ርቀት ተወንጫፊ መሳሪያዎች በመታገዝ አጻፋ በመስጠት የሚመክቱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

ዜሌነስኪ አያይዘውም “በአንጻሩ የወታደሮቻችንና የህዝባችንን ህይወት መታደግ መቻላችን እኩል ድርሻ ይኖረዋል፡፡ የፈረሰውን ግንብ መልሰን እንገነባለን። መሬታችንን እናስመልሳለን። ከሁሉም በላይ ደግሞ የህዝባችን ደህንነት መጠበቅ አለበት” ብለዋል፡፡

የዩክሬን ጦር ሰራዊት በሰው ኃይልና በመሳሪያ ብልጫ ያላቸውን የሩሲያ ወታደሮች በመከላከሉ ሥራ መቀጠሉ “አደገኛ ውጤት ያስከትላል” ሲሉ የቀሩትን ወታደሮች ከሊስቻንክስ ግዛት ለማስወጣት መወሰኑን ትናንት እሁድ አስታውቋል፡፡

የዩክሬን ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ ለአጋሮቻቸው ባቀረቡት ጥሪ ከሩሲያ ጦር ጋር የሚመጣጠን ዘመናዊ የጦር መሳሪያ በመሰጠት እንዲያግዟቸው ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡

ሩሲያ አራተኛ ወሩን ያስቆጥጠረው ወረራዋን እንደጀመረች ዜለነስኪን ከሥልጣን ለመገልበጥ አለያም ኪየቭን ለመቆጣጠር የነበራት ዕቅድ ከከሸፈባት በኋላ መላ ትኩረቷን የሉሃንስክ እና ዶኔትስክ ግዛቶችን የሚያካትትተውን የዶባናስ ክልልን በመቆጣጠሩ ላይ አድርጋለች፡፡

የዩክሬን አሁንም በዶኔትስክ በርካታ ከተሞችን እንደተቆጣጠረች ነው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሉሃንስክ አገረ ገዥ ሴርሂ ሃይዳይ ለሮይተር በሰጡት አስተያየት ሊሲቻንስክን ማጣት ከባድ መሆኑን አምነው ዩክሬይን ማሳካት ያለባት ከተሞችን ለመያዝ መዋጋት ብቻ ሳይሆን ማሸነፍ ያለባት ጠቅላላውን ጦርነት ነው ብለዋል።

በሌላ ዜና ስዊዘርላንድ ዛሬና ነገ ማክሰኞ ዩክሬንን መልሶ ለመገንባት ምን ያስፈልጋል በሚል ሃሳብ ላይ ያተኮረ ጉባኤ በማስተናገድ ላይ ነች።

በሉጋኖ እየተካሄደ ያለው ጉባኤ ከበርካታ አገራት የመጡ መሪዎችን፣ ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች እና እንዲሁም ከግሉ ዘርፉ የተወጣጡ አካላትን አካቷል፡፡

በስዊዘርላንድ የዩክሬኑ አምባሳደር አርቴም ሪብቼንኮ “ጉባኤው አገራቸውን መልሳ ለመገንባት የሚያግዝ ፍኖተ ካርታ ለማውጣት ይረዳል” ብለዋል፡፡

ዜሌነስኪ በበኩላቸው ለተሰብሳቢዎቹ የቪዲዮ መልዕክት ያሰማሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር ዴኒስ ሽሚሃይል በስብሰባው በአካል ተገኝተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG