በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ ኃይሎች ወደዩክሬን ሲቪየሮዶኔትስ ከተማ እየገፉ ነው


ዩክሬን በዶንባስ ምሥራቃዊ ከሲየቪዬሮዶኔትስክ ከተማ የዩክሬን እና የሩሲያ ጦርነት አካባቢው በተኩስ ጭስ ተሞልቶ ይታያል እአአ ሰኔ 14/2022
ዩክሬን በዶንባስ ምሥራቃዊ ከሲየቪዬሮዶኔትስክ ከተማ የዩክሬን እና የሩሲያ ጦርነት አካባቢው በተኩስ ጭስ ተሞልቶ ይታያል እአአ ሰኔ 14/2022

የሩሲያ ኃይሎች ከሲቪየሮዶኔትስክ ጋር የሚያገናኘውን የመጨረሻውን ድልድይ እንዳፈረሱት የዩክሬን ባለሥልጣናት ገለጹ። በዚህም የተነሳ በቅርብ ሳምንታት ዋና የውጊያ ግንባር ሆና ከሰነበተችው የምስራቅ ዩክሬን ከተማ አሁንም ያሉ ሲቪሎችን ማውጫ መንገድ እንደሌለ ገልጠዋል። ሩሲያውያኑ መሃል ከተማዋን ለመያዝ እየሞከሩ መሆናቸውን የዩክሬን የጦር ኃይል አስታውቋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ዶንባስን ለመቆጣጠር እየተካሄደ ያለው ጦርነት በአውሮፓ ከባድ ጦርነቶች አንዱ ሆኖ በታሪክ ይመዘገባል ብለዋል። በዚህ ውጊያ የምንከፍለው ዋጋ እጅግ ከፍተኛ እና እስፈሪ ነው ያሉት ዜሌንስኪ አጋር ሀገሮች ዘመናዊ መድፎችን እንዲልኩ እንደገና ተማጽነዋል።

የፕሬዚዳንት አማካሪ ሚኻይሎ ፖዶልያክ ትናንት በሰጡት ቃል ነገ ረቡዕ ብረሰልስ ላይ የሚሰባሰቡት በዩናይትድ ስቴትስ የሚመራውን አገናኝ ቡድን አባላት ስለመሳሪያ ዕርዳታው የሚደርሱበትን ውሳኔ እንጠብቃለን ብለዋል። በዚህ ጦርነት ለማሸነፍ ከባድ መሳሪይ ያስፈልገናል ሲሉ አሳስበዋል።

XS
SM
MD
LG