በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን የተጨማሪ የጦር መሳሪያዎችን አፋጣኝ ድጋፍ ጠየቀች


የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን
የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን

- ሎይድ ኦስተን 20 አገሮች ተጨማሪ የደህንነት እርዳታ እየላኩ ነው አሉ

የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ድሚትሮ ኩሌባ የሩሲያ ኃይሎችን ለመዋጋት ሌሎች መንግሥታት ተጨማሪ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ዩክሬን እንዲልኩ አሳሰቡ፡፡ ሚኒስትሩ ዛሬ ማክሰኞ ባወጡት የትዊት መልዕክት “ዩክሬን የሚያስፈልጋትን የጦር መሣሪያ ሁሉ አግኝታለች ብሎ ከወዲሁ ለመደምደም ጊዜው ገና ነው” ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ አያይዘውም “ሩሲያ በዶናባስ እያደረሰችው ያለው ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወዲህ በአውሮፓ ምድር የታየ ትልቁ ጥቃትና የጭካኔ ጦርነት ነው” ሲሉ ገልጸውታል፡፡፡

“ሁሉም አጋሮች በተለይ የጦር መሳሪያና ጥይቶችን በተለይ MLRS የተባሉ የሮኬት ተኳሾ፣ የረጅም ርቀት መድፎችና APC የተባሉትን ብረት ለበስ የሰዎችና የጦር መሳሪያ ማጓጓዣ ተሽከርካሪዎችን አቅርቦት ማፋጠን አለባቸው” ሲሉም ሚኒስትሩ አሳስበዋል፡፡

የኩሌባ ተጨማሪ የወታደራዊ መሳሪያዎች እርዳታ ጥሪ የመጣው፣ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር፣ ሎይድ ኦስትን፣ ወደ 20 የሚሆኑ አገሮች ወደ ዩክሬን አዳዲስ የደህንነት እርዳታዎችን እየላኩ መሆኑን ካስታወቁ በኋላ ነው፡፡

ዛሬ ከጃፓና ህንድና አውስትራሊያ መሪዎች ጋር የተገናኙት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ በዩክሬን ያለው ጦርነት ከአውሮፓ ጉዳይ የዘለለ ዓለም አቀፋዊ ጉዳይ ነው” ሲሉ ገልጸውታል፡፡

“የሩሲያ ወረራ እስከቀጠለ ድረስ ዩናትድ ስቴትስ ሌሎች አገሮችንም ጭምር በማስተባበር የምትሰጠውን ድጋፍ ሳታቋርጥ ትቀጥልበታለች፡፡” ብለዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፣ ባለፈው ሰኞ ባስተላለፉት የቪዲዮ መልዕክት፣ ጦርነቱ ከተጀመረ አንስቶ፣ በሶስት ወራት ውስጥ፣ ሩሲያ 1ሺ500 ሚሳዬሎችን ዩክሬን ላይ መተኮሷን ገልጸው፣ ከዚህ ውስጥ 1ሺ474 የሚደርሱት ሰላማዊ ሰዎችን ያጠቁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

መከላከያ ሚኒስትሩ ኦስተን 20 አገሮች ለዩክሬን ተጨማሪ የደህንነት እርዳታ እየላኩ ነው አሉ

ወደ 20 የሚደርሱ አገሮች ለዩክሬን በርካታ ነገሮችን የተካተቱበትን ተጨማሪ የደህንነት እርዳታ እየላኩ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን አስታወቁ፡፡

ሎይድይህን የገለጹት በዩክሬን መከላከያ ጉዳይ እየተገናኘ የሚመክረው ቡድን ሁለተኛውን ስብሰባ በበይነ መረብ ላይ ካካሄደ በኋላ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ሎይድ “በርካታ አገሮች እጅግ ወሳኝ የሆኑ የከባድ መሳሪያ ጥይቶችን፣ የባህር ዳርቻ መከላከያ መሳሪያዎችን፣ ታንኮችን እና ሌሎች የጦር ተሽከርካሪዎችን እየሰጡ ነው፡፡ ሌሎቹም ለዩክሬናውያኑ ኃይል ለማሰልጠንና ጦሩንም በዘላቂነት ለማደርጀት እርዳታዎችና ሥልጠናዎችን ለመስጠት አዳዲስ ቃሎችን እየገቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዴንማርክ ለዩክሬን ኃይሎች ሃርፑን የተሰኘውን የሚሳኤል ማስተኮሻ እንደምትሰጥ ያስታወቀች ሲሆን የቼክ ሪፐብሊክም ተዋጊ የማጥቂያ ሂሊኮፕተሮችን ታንኮችንና ሮኬቶችን ለመስጠት ቃል ገብታለች፡፡

የትናንቱ ስብሰባ ኦስትሪያ ኮሎምቢያ እና አየርላንድን ጨምሮ፣ 47 አገሮች በበይነ መረብ የተሳተፉበት መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ የጠቅላይ ኤታማዦር ሹሙ ማርክ ሜሊ ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG