ተጨማሪ ሰላማዊ ሰዎችን በተከበበችው የዩክሬና ማሪዮፑል ከተማ ከሚገኘው የኦቭስታል የብረታ ብረት ፋብሪካ ለማውጣት የሚደረገው ጥረት መጀመሩ ተነገረ፡፡
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አንድሪ ይርማክ ዛሬ ዓርብ በሰጡት መግለጫ “በአሁኑ ወቅት ቀጣይ ሂደታችን የሆነው በኦቮስታል የሚገኙ ሰዎቻችንን የማዳን ሥራ እየተከናውነ ነው” ብለዋል፡፡
ይሁን እንጂ እስካሁን ያለው ዝርዝር መረጃ ትንሽ ነው ያሉት አንድሪ “ስለ ውጤቱ ያለው መረጃ ወደ ኋላው ላይ የሚገለጽ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ትናንት ሀሙስ በተቋሙ ውጊያው መቀጠሉ ተነግሯል፡፡
ሩሲያ በተቋሙ ውስጥ ያሉትና በግምት 200 ይደርሳሉ የተባሉትን ሰላማዊ ሰዎች እንዲወጡ ለማድረግ በቀኑ ከፍለ ጊዜ የተኩስ አቁም ይደረጋል ያለች ቢሆንም፣ የሩሲያ ወታደሮች ወደ ውስጥ ዘልቀው መግባታቸው፣ የዩክሬን ተዋጊዎች በቦታቸው እንደነበሩ ተመልክቷ፡፡
የሩሲያ ኃይሎች በኦዞቭ ባህር ዳርቻ ያለውን መላውን ማሪዮፑል የተቆጣጠሩ ቢሆንም የብረታብረት ፋብሪካውን አስካሁን መቆጣጠር አልቻሉም፡፡ የሩሲያ ኃይሎች በአካባቢው ላለፉት 10 ሳምንታት ተከታታት ጥቃ በማድረስ ላይ መሆናቸው ተመልክቷል፡፡
የዩክሬን አገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር አማካሪ አንቶን ጌራስቼንኮ የሩሲያ ወታደሮች የቦታውን ዝርዝር ንድፍ በሚያውቅ ውስጥ አዋቂ የኤሌክትሪክ ባለሙያ አማካይነት ባለቸው መረጃ እየተረዱ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሩሲያ ወደ ማዕከሉ መግባቷን ያስተባበለች ሲሆን ዩክሬናውያኑን ሰላማዊ ሰዎች እንዳይወጡ በማድረግ ከሰዋቸዋል፡፡
በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከተቋሙ ውስጥ ወደ 100 የሚቆጠሩ ሰላማዊ ሰዎችን ማውጣት መቻሉ ተመልክቷል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለም የዓለም ምግብ ድርጅት ዩክሬን ውስጥ በጦርነቱ ለተጎዱና በጦርነቱም የተነሳ ወደ ሞልዶቫ ለተፈናቀሉ ዩክሬናውያን መርጃ የ26.4ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ከአውሮፓ ህብረት ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
የዓለም ምግብ ድርጅት ከ7.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ዩክሬን ውስጥ መፈናቀላቸውን ገልጾ በአገሪቱ ግማሽ የሚያህሉት ዩክሬናውያን የሚበላ በቂ ነገር ስለማግኘታቸው ስጋት የገባቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡