በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በማሪዮፑል ለዕለቱ የጠየቀችውን የተኩስ ማቆም ዘለንስኪ የረጅም ጊዜ እንዲሆን ጠየቁ


በማሪዮፖል ውስጥ በግጭቱ የወደመ የመኖሪያ ሕንፃ አካባቢ
በማሪዮፖል ውስጥ በግጭቱ የወደመ የመኖሪያ ሕንፃ አካባቢ

ሩሲያ ዛሬ ሀሙስ የዩክሬን ወታደሮች አሁን ድረስ ከሚገኙበት የብረታ ብረታ ፋብሪካው ውጭ ያለውን ቦታ ሁሉ በተቆጣጠረችበት በዩክሬኗ የማሪዮፑል ከተማ ተኩስ እንዲቆም ቃል ገብታለች፡፡ የተባበሩት መንግሥታትም ሰላማዊ ሰዎችን ከስፍራው ለማውጣት እየሰራ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ሩሲያ ከኦዞቭስታል ፋብሪካ ሌሎችም ሰላማዊ ሰዎች እንዲወጡ ለማስቻል ዛሬ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ተግባራዊ የሚሆነው የተኩስ አቁም ነገ ዓርብና ቅዳሜም ቀጥሎ እንደሚውል ገልጻለች፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎደሚር ዘለነስኪ ዛሬ ሀሙስ ጧት በሰጡት መግለጫ በማሪዮፑል የቀሩትን ሰላማዊ ሰዎች ለማስወጣት ዘለግ ያለ የተኩስ አቁም ጊዜ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

ዘለነስኪ አያይዘውም “ሰዎችን ከምድር ቤት ወይም ከዚያ የምድር ውስጥ መጠለያ እንዲወጡ ለማድረግ ብቻ እንኳ ብዙ ጊዜ ይፈጃል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታ ፍርስራሾችን ጠራርጎ ለማንሳት ትላልቅ መሳሪያዎችን መጠቀም አንችልም፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በዋሽንግተን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ሩሲያ ስለተናገረችው የተኩስ አቁም ጥርጣሬ ያላቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

“አሁን በቋሚነት የምናስተውለው በቅርብ ጊዜ ውስጥም የተመልከትነው በሩሲያ ፌድሬሽ በኩል ለሰብአዊነት በሚል መልኩ ለአፍታ ቆም ማድረግና ወዲያው ደግሞ ማሪዮፑልን ጨምሮ በተከበበው ስፋራ ባሉት ሰላማዊ ሰዎች ላይ ጥቃትን መሰዘርና በከባድ መሳሪያ መደብደብን ነው፡፡”

የተባበሩት መንግሥታት ትናንት ረቡዕ ከማሪዮፑል ማኑሽ፣ በርዲያንስክ፣ ቶክማክ እና ቫስይሊቭካ ከ300 በላይ ሰላማዊ ሰዎች መውጣታቸውን አስታውቋል፡፡

“ከማሪዮፑልና አካባቢው ሰላማዊ ሰዎች የሚወጡበት ይህ ሁለተኛው ዙር እንቅስቃሴ ጠቃሚ ቢሆንም በጦርነቱ መካከል መውጫ አጥተው የቀሩ ሰላማዊ ሰዎች ሁሉ ወጥተው ወደ ፈለጉበት አቅጣጫ መሄድ ይኖርባቸዋል፡፡”

የቤላሩስ ልምምድ

የቤላሩስ ፕሬዚዳንት አሌክዛንደር ሉካሼንኮ ለአሶሼይትድ ፕሬስ እንደተናገሩት የሩሲያ ወታደሮች በዩክሬን የሚያደርጉት ነገር “በዚህ አቅጣጫ ይወሰዳል” ብለው አለመገመታቸውን ገልጸው “ዩክሬን ሩሲያን መተንኮሷን” እና ለሰላም ንግግር ፍላጎት የሌላት መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የሩሲያ ኃይሎች እኤአ በየካቲት 24 ከጀመሩት ወረራ በፊት፣ ቤላሩስን በጋራ ወታደራዊ ልምድድ ስም እንደመረማመጃ የተጠቀሙበት ሲሆን ፕሬዚዳንት ፑቲንም ዩክሬንን የሚያጠቁ ስለመሆኑ አስተባብለዋል፡፡

ቤላሩስ በዚህ ዛምንት የራሷን ወታደራዊ ልምምድ አካሂዳለች፡፡ ፕሬዚዳን ሉካሼንኮ ግን ይህ ምንም ስጋት አለመፍጠሩን ይናገራሉ፡፡

“ማንንም አናስፈራራም፣ ማንንም አናስፈራራምም አናደርገውምም፡፡” ሲሉ ለአሶሼይትድ ፕሬስ የተናገሩት ሉካሼንኮ “ከሁሉም በላይ እኛ ማስፈራራት አንችልም ምክንያቱም ማን እንደሚቃወመን እናውቃለን፡፡ እዚህ በምዕራቡ በኩል አንድ ዓይነት ግጭት ወይም አንድ አይነት ጦርነት ማስነሳት የቤላሩስ ፍላጎት አይደለም፡፡ ስለዚህ ምዕራብውያን በሰላም መተኛት ይችላሉ፡፡” ብለዋል፡፡

የብሪታኒያ መከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ሀሙስ እንዳስታወቀው ሩሲያ የምታደርገው ነገር በቤላሩስ “በዩክሬን ላይ የተደቀነውን አደጋ በማጉላት” በርካታ የዩክሬን ኃይሎች በሰሜን የአገሪቱ ክፍል እንዲቆዩ በማድረግ ወደ ምስራቅ ዩክሬን ብዙ ወታደሮችን እንዳያሰማሩ ለማድረግ ነው፡፡

ውጊያ በምስራቅና በደቡብ

በማሪዮፑል ኦዞቭስታል ብረታ ብረት ፋብሪካ ትናንት ረቡዕ ውጊያው ተጠናክሯል ፡፡

የማሪዮፑል ከንቲባ ቫዲም ቦይቼንኮ “ሩሲያውያኑ ፋብሪካውን ከከባድ መሳሪያ ጀምሮ ኮክሪትን ከ3 እስከ 5 ሜትር ነድሎ ሊዘልቅ እስከሚችል ቦምብ ባገኙት ነገር ሁሉ እየደበደቡ ነው” ብለዋል፡፡

የዩክሬን ተዋጊዎች ፋብሪካውን እየተከላከሉ ሲሆን ሩሲያውኑም ወደ ስፍራው መግባታቸውን ተናግረዋል፡፡ ሩሲያ ግን አስተባብላለች፡፡

አንድ ከፍተኛ የዩናትይድ ስቴትስ ባለሥልጣን በምስራቅ ዩክሬን በዶናባስ በኩል ያለው የሩሲያ ወታደራዊ ግስጋሴ “ ተገቷል...አዝጋሚና ወጥትነት ያለው አይደለም፡፡” ብለዋል፡፡

ሩሲያ በቀን ከ40 እስከ 50 የሚደርሱ ሚሳዬሎች ትተኩሳለች ፡፡ በዩክሬን ውስጥ ለመብረር ግን አሁንም ትጠነቀቃለች፡፡

የሩሲያ ኃይሎች ወደ ምስራቅ ዩክሬን ወደ ክራማስቶርስክ እና ሰቨሮዶነትስክ አካባቢዎች የሚያደርጉት ግስጋሴ ከፍተኛ መከላከል እንደገጠመው የዩክሬን ባለሥልጣኖች ተናግረዋል፡፡

በዩክሬን የአደጋ ጊዜ ማስጠንቀቂያ ደወሉ በጣም ይንጫረር በነበረበት ትናንት ረቡዕ ምሽቱን በማዕከላዊ ዩክሬን በኪየቭ አቅራቢያ ቸርካሲ እና ዲንፕሮ እንዲሁም በደቡብ ምስራቅ ዛፖሪዝዝያ ጥቃቶች መሰንዘራቸው ተነገሯል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽነር ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌየን በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ከሩሲያ ወደ አውሮፓ የሚመጣውን የድፍድፍ ነዳጅ በስድስት ወር እንዲሁም የተጣራውን ነዳጅ ደግሞ በሚቀጥለው ዓመት መጨረሻ ጀምሮ ለማቆም የሚያስችለውን ማዕቀብ ጨምሮ በሩሲያ ላይ የሚጣለውን ዘርፈ ብዙ ማዕቀብ በትናንትናው እለት ይፋ አድርገዋል፡፡

ማዕቀቡ በሁሉም የአውሮፓ ህብረት አባል አገሮች መጽድቅ እንደሚኖበት ተነግሯል፡፡

ቫን ደር ሌይን ስለዚሁ ለአውፓር ህብረት ምክር ቤት ሲናገሩ” እዚህ ጋ ግልጽ መሆን እፈልጋለሁ፣ አንዳንድ አገሮች በሩሲያ ነዳጅ ላይ ጥገኛ ስለሆኑ ቀላል ይሆናል ማለት አይደለም ይሁን እንጂ ግን ይህን ነገር ማድረግ አለብን” ብለዋል፡፡

እርምጃው የአውሮፓ አገሮች ከሩሲያ ይመጣ በነበረው ነዳጅ ሳቢያ በዓለም የነዳጅ ገበያ ላይ ሊፈጠር የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ ሌሎች አማራጮችን እንዲመለከቱ የሚረዳቸው ሲሆን በሩሲያም ላይ ተጨማሪ ጫና ለመፍጠር ያስችላል ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG