በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን ፕሬዚዳንት የተመድ ዋና ጸሃፊን ያነጋግራሉ


ዋና ፀኃፊ ጉቴሬዥ የሩሲያ ወታደሮች ለቅቀው ከወጡ በኋላ የበርካት ሰላማዊ ሰዎች አስከሬኖች የተገኙባትን ቡቻን ጨምሮ ኪየቭ አቅራቢያ ያሉ አካባቢዎችን ጎብኝተዋል።
ዋና ፀኃፊ ጉቴሬዥ የሩሲያ ወታደሮች ለቅቀው ከወጡ በኋላ የበርካት ሰላማዊ ሰዎች አስከሬኖች የተገኙባትን ቡቻን ጨምሮ ኪየቭ አቅራቢያ ያሉ አካባቢዎችን ጎብኝተዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ የተመድ ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥን ዛሬ ሃሙስ ተቀብለው ያነጋግራሉ። የሩሲያ የኤነርጂ አቅርቦት አንዲታገድ ዩክሬን ጠይቃለች። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለዩክሬን የሚሰጥ ወታደራዊ ኢኮኖሚያዊ አና ሰብዓዊ እርዳታ እቅድ አያዘጋጁ ናቸው።

ዋና ፀኃፊ ጉቴሬዥ የሩሲያ ወታደሮች ለቅቀው ከወጡ በኋላ የበርካት ሰላማዊ ሰዎች አስከሬኖች የተገኙባትን ቡቻን ጨምሮ ኪየቭ አቅራቢያ ያሉ አካባቢዎችን ጎብኝተዋል። በቡቻው ጉዳይ የጦር ወንጀል ምርመራ አንዲከፈት ጥሪ መቅረቡ ይታወሳል። የተመዱ ዋና ፀኃፊ ጉቴሬዥም ሩሲያ የዓለም አቀፉ ወንጀል ፍርድ ቤት አይሲሲ በሚያካሂደው ምርመራ አንድትተባበር ጥሪ አቅርበዋል።

“አይሲሲን ሙሉ በሙሉ አደግፋለሁ፣ የሩሲያ ፌዴሬሽን የአይሲሲን ምርመራ አንዲቀበል አና አንዲተባበር አማፀናለሁ፣ ነገር ግን ስለጦር ወንጀል ስናወራ ጦርነት በራሱ ወንጀል መሆኑ መዘንጋት የለብንም” ብለዋል።

ጉቴሬዥ ዩክሬን አንደገቡ የሰብዓዊ ረድዔት ድጋፎችን ለማስፋፋት አና ሲቪሎች ከግጭት አካባቢዎች የሚወጡበት መንገድ አንዲመቻች የሚፈልጉ መሆናቸውን ገልፀዋል። በእነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ በሩሲያ ቆይታቸው ከፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን አና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ተወያይተውበታል።

ጉቴሬዥ በትዊተር ባወጡት ጽሁፋቸው “ጦርነቱ ለዮክሬንም ለሩሲያም ለመላው ዓለምም ሲባል በፍጥነት ቢያከትም ነው የሚሻለው” ብለዋል።

ዛሬ የዩክሬን ፕሬዚዳንታዊ አማካሪ ሚኻይሎ ፖዶሊያክ በሰጡት ቃል

“የሩሲያ ዋናው የኤነርጂ ኢንዱስትሪ የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ መታገዱ አይቀርም” ብለዋል።

ሩሲያ ለፖላንድ አና ለቡልጋሪያ ጋዝ መላክ ትናንት አቁማለች። ዋይት ኃውስ ሩሲያ ይህን አንደምታደርግ የተጠበቀ ጉዳይ ነው ብለዋል።

የዋይት ኃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ ከአውሮፓ ሀገሮች ስንነጋገርበት የቆየነው ባለፈው ሃያ አራት ሰዓት ውስጥም ከፖላንድ አና ከቡልጋሪያ መሪዎች የተነጋገርነው በዚህ ምክንያት ነው ብለዋል። የአውሮፓ የጋዝ አቅርቦት ምንጭ አንዲሰፋ ስንሰራበት ቆይተናል ሲሉም አክለዋል፤

ፕሬዚዳንት ባይደን “ዩክሬናውያን ከሩሲያ የጭካኔ ወረራ ሀገራቸውን አና ነጻነታቸውን አንዲከላከሉ ስለሚሰጥ ድጋፍ ዛሬ ንግግር አንደሚያደርጉ ዋይት ኃውስ አስታውቋል። ትናንት የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር በሰጠው ቃል ዘጠና ረጅም ርቀት ተወንጫፊ መድፎች ዩክሬን መግባታቸውን አና የየመሳሪያው ሥልጠና ዝግጅትም መጠናቀቁን ገልጿል። የኔቶ ዋና ጸሀፊ ዬንስ ስቶልትንበርግ ዛሬ አንደገለጹት በህብረቱ አባል ሀገሮች ለዩክሬን አስካሁን የተሰጠው ወይም ቃል የተገባው ወታደራዊ ድጋፍ ስምንት ቢሊዮን ዶላር መግባቱን ገልጸዋል።

የሩሲያ ወረራ ፊንላንድ አና ስዊድን ህብረቱን ለመቀላቀል አናመልክክት የሚለውን ሃሳብ አንዳጫረባቸው ሲታወቅ ስቶልትንበርግ ሀገሮቹ እርምጃውን ከወሰዱ ሂደቱ በፍጥነት ይጠናቀቅላቸዋል ብለዋል።

XS
SM
MD
LG