በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ለፖላንድ እና ቡልጋሪያ ጋዝ መላክ አቆመች


ፎቶ ፋይል፦ የሩሲያ የነዳጅ ኩባኒያ ጋዝፕሮም በሴንት ፒተርስበርግ
ፎቶ ፋይል፦ የሩሲያ የነዳጅ ኩባኒያ ጋዝፕሮም በሴንት ፒተርስበርግ

ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ ለዩክሬን የሚሰጠውን ባፋጣኝ ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ እየሰሩ ነው፤ ዲፕሎማቶች በበኩላቸው ከዩክሬን ሲቪሎች መውጣት እንዲችሉ እና የተኩስ አቁም ሥምምነት እንዲደረስ ጥረት እያደረጉ ናቸው።

የሩሲያው የነዳጅ ኩባኒያ ጋዝፕሮም ለፖላንድ እና ለቡልጌሪያ ጋዝ መላክ አቋረጠ። ይህ እርምጃዋ ሩሲያ ዩክሬንን በመውረሯ የተቀሰቀሰው ኢኮኖሚያዊ ትግል አካል ነው። ብዙዎች የአውሮፓ ሀገሮች አብዛኛውን የነዳጅ እና የጋዝ አቅርቦታቸውን የሚገዙት ከሩሲያ ሲሆን በራሴ ገንዘብ በሩብል ክፈሉኝ ማለቷ ይታወሳል። እናም ዛሬ ጋዝፕሮም ፖላንድ እና ቡልጌሪያ የጠየቅነውን አላደረጉም ስለዚህ ጋዝ አንልክም ብሏል። የሁለቱ ሀገሮች ባለሥልጣናት የሩሲያ እርምጃ ውል የጣሰ ነው ብለዋል።

ሩሲያ በጋዟ ተጠቅማ ልታስፈራራን መሞከሯ ነው ያሉት የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደረ ሊየን "እኛም ይህ እንደሚመጣ አውቀን ወደም ብለን ተዘጋጅተንበታል፤ የህብረቱን የተቀናጀ ምላሽ እያሰናዳን ነን" ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ ለሊቱን ዩክሬን ውስጥ የሚሳይል ጥቃቶች አድርሰን ሃምሳ ዘጠኝ ዒላማዎች አውድመናል ሲል አስታውቋል። ከዒላማዎች መካከል ዩናይትድ ስቴትስ እና ሌሎችም አጋሮቿ የላኩላቸው የጦር መሳሪያዎች እና ጥይቶች የተከማቹበት መጋዘኖች እንዳሉባቸው አስታውቃለች።

ሩሲያ ለፖላንድ እና ቡልጋሪያ ጋዝ መላክ አቆመች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:53 0:00

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ዩናይትድ ስቴትስ እና አጋሮቿ ዩክሬንን ለመርዳት እና በሩሲያ ኢኮኖሚ ላይ ተጽዕኖውን ለማጠናከር በአፋጣኝ እንደሚንቀሳቀሱ ፍንጭ ሰጥተዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ለመወሰኛ ምክር ቤት የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ ባደረጉት ገለጻ መጀመሪያ ላይ ወደ ዩክሬን የጦር መሳሪያ እርዳታ ለመላክ ሳምንታት ይወስድ እንደነበር ገልጸዋል። አሁን ግን በሦስት ቀን ውስጥ እየተላከላቸው ነው ብለዋል።

አስከትለውም ሚኒስትር ብሊንክን እሳቸው እና የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ባለፈው ሳምንት መጨረሻ በኪየቭ ከዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ የተነጋገሩ ሲሆን "ያስፈልጉናል ባሉት ሁለቱ ሀገሮች በአብዛኛው ተስማምተውበታል የጠየቁትን መስጠት የምንችል ይመስለኛል" ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ጀርመን ለመጀመሪያ ጊዜ ከባድ የጦር መሳሪያ ለዩክሬን እንደምትልክ ትናንት ያስታወቀች ሲሆን የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስተን ጀርመን ውስጥ ከአርባ አገሮች ባለሥልጣናት ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ባሰሙት ንግግር "የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን መላው ዓለም እንዲህ በፍጥነት እና በቁርጠኝነት ከዩክሬን ጎን ይቆማል ብለው ፈጽሞ ያልጠበቁት ነገር ነው" ብለዋል።

የጀርመንን እርምጃ ዋይት ሀውስ በሩሲያ ወረራ ላይ ካሁን ቀደም ከነበረው የጠነከረ አንድነት የሚያንጸባርቅ ብሎታል።

XS
SM
MD
LG