በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በምስራቅ ዩክሬን ውጊያው ተባብሷል


ፎቶ ፋይል፦ በዩክሬን እና ሩሲያ ግጭት የተጎዳ የመኖሪያ ሕንፃ፤ ደቡባዊው የወደብ ከተማ፣ ማሪፖል ሚያዚያ 19/2022
ፎቶ ፋይል፦ በዩክሬን እና ሩሲያ ግጭት የተጎዳ የመኖሪያ ሕንፃ፤ ደቡባዊው የወደብ ከተማ፣ ማሪፖል ሚያዚያ 19/2022

ዩክሬን ዛሬ ረቡዕ በሰጠችው መግለጫ በጦርነት ከወደመችው ማሪዮፑል ከተማ ሰላማዊ ሰዎችን ለማስወጣት ከሩሲያ ጋር የቅድሚያ ስምምነት የተደረሰ ቢሆንም ሩሲያ ግን በድጋሚ በከተማዪቱ የቀሩ ወታደሮች አሁንም እጃቸውን እንዲሰጡ አሳስባለች ስትል አስታወቀች፡፡

የዩክሬን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አርያና ቪርሸክ ሰላማዊ ሰዎችን ለማስወጣት የተከፈተው መንገድ ህጻናት፣ ሴቶችና አረጋውያንን ለማስወጣት የታለመ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ቪርሸክ በፌስቡክ ገጻቸው በሰጡት ተጨማሪ ማብራሪያ “ዛሬ ትኩረታችንና ጥረታችንን የምናደርገው በማሪዮፑል ባለው አደገኛ የሰብአዊ ቀውስ ሁኔታ ላይ ነው” ብለዋል፡፡ በአገሪቱ ባላፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ሰላማዊ ሰዎች የሚወጡበትን መንገድ ለመክፈት አለመቻሉን ቪርሸክ አስታውቀዋል፡፡

ሩሲያ በማሪዮፑል የሚገኙ የዩክሬን ተዋጊዎች እጃቸውን እንዲሰጡ የሰጠችው ቀነ ገደብ ዛሬ ረቡዕ ነበር፡፡ ዩክሬን ግን አልተቀበለችውም፡፡ የማክሰኞውም ቀነ ገደብ ያለፈው አንድም የዩክሬን ወታደር ለደህንነቱ ሲል የሩሲያን ቀነ ገደብ ባለመቀበሉ ነበር፡፡ የማሪዮፑል ዜና የመጣው ሩሲያ ስትራቴጂክ ከተማ በሆነቸው ዶንባስ ግዛትን ወታደራዊ ይዞታዋን ማጠናከር በቀጠለችበት ሁኔታ ነው፡፡

የእንግሊዝ የመከላከያ ሚኒስቴር ዛሬ ረቡዕ ባወጣው መግለጫ የሩሲያ ኃይሎች የዩክሬንን መከላከያ ሰብረው ለማለፍ በመሞከራቸው በክልሉ ያለው ውጊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

“ሩሲያ በዩክሬን ከተሞች የምታካሂደው ጥቃት የዩክሬንን የሰው ኃይሏን መሳሪያዋን እንደገና አጠናክራ ወደ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል የምታደርገውን እንቅስቃሴ ለማጨናገፍ ነው” ሲል የሚኒስቴሩ መግለጫ አመልክቷል፡፡

የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቻርለስ ማይክል ይፋ ባልተደረገ ጉብኝት በድንገት ኪየቭ ገብተዋል፡፡ በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ድጋፍ ለማሳየት ወደ ዩክሬን ከተጓዙ የአውሮፓ መሪዎች መካከል አንዱ ሆነዋል፡፡ ማይክል ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት

“በነጻዪቱና ዲሞክራሲያዊቱ አውሮፓ መሃል” ብለዋል፡፡ ከሰዓታት በፊት የኖርዌ መከላከያ ሚኒስቴር 100 የሚደርሱ አጭር የአየር መከላከያ መሳሪያዎችን ለዩክሬን መላኩን አስታውቋል፡፡

ሚኒስቴሩ በመግለጫው መሳሪያዎቹ በኖርዌይ የሚሰጡት አገልግሎት ያበቃ ቢሆንም አሁንም ቢሆን “ዘመናዊና ውጤታማ መሳሪያዎች” በመሆናቸው ለዩክሬን ኃይሎች ጥቅም ይሰጣሉ ብሏል፡፡ የዋይት ኃውስ የፕሬስ ዋና ጸሀፊ ጄን ሳኪ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የብሪታኒያ፣ ካናዳ፣ አውሮፓ ህብረት፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ጣልያን፣ ጃፓን፣ ኔቶ፣ ፖላንድ እና ሩማንያ መሪዎች፣ ትናንት ሀሙስ፣ ለኪየቭ ተጨማሪ የጦር መሳሪያዎችና የደህንነት እርዳታ ለማድረግ፣ መነጋገራቸውን አስታውቀዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በዚህ ሳምንት በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀቦችን ለመጣል እያሰበች መሆኑንም ሳኪ አስታውቀዋል፡፡ ባይደንና የኔቶ አጋሮች ትናንት ማክሰኞ በደረሱበት ስምምነት መሰረት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑትን የኃይል ምንጮችን እንደ መሳሪያ በመጠቀም የአሜሪካና የአውሮፓ የሚገኙ ቤተሰቦችን ለመጉዳት የሚያደርጉትን ጥረት ለማቆም ለሚቀጥሉት ስድስት ወራት በየቀኑ 240 ሚሊዮን በርሜል ነዳጅ ወደ ገበያው ለመልቀቅ መስማማታቸው ተመልክቷል፡፡

ዶናባስ ጥቃት

የዶናባስ ግዛትን በመደብደብ ላይ የምትገኘው ሩሲያ ትናንት ማክሰኞ ምስራቅ ዩክሬንን ለመቆጣጠር አዲስ ጥቃት መሰንዘሯን አስታውቃለች፡፡ ዩክሬን ግን ግዛቱን እየተከላከለች መሆኑን አስታውቋ አንዳንዶቹን ጥቃቶች መቀልበስ መቻሏን ገልጻለች፡፡

“የዘመቻው ሌላኛው አካል አሁን ተጀምሯል” ያሉት የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌይ ላቫሮቭ የሞስኮ ዓላማ በምስራቅ የሚገኙ ዶኔትስክ እና ሉሃንስክን ግዛቶች “ፍጽሙ ነጻ” ማውጣት ነው ብለዋል፡፡

በዋሽንግተን የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር ከፍተኛ ባለሥልጣን አሁን የተጀመረው አዲሱ የሩሲያ ጥቃት የመጭው ትልቅ ውጊያ መግቢያ ነው ብለዋል፡፡ ምክንያቱም “ጦርነቱ ለተወሰነ ጊዜ ሊቀጥል ስለመቻሉ ይህ ማሳያ ነው፣ ሁለቱም ወገኖች እዚህ ነገር ውስጥ ጨርሰው እየተነከሩበት ነው ገና በደንብ ጠልቀው ይገቡበታል፡፡” ባለሥልጣኑ ከሩሲያ ኃይል ጋር ሲነጻጸር ዩክሬን በሰው ኃይል ተበልጣለች ይላሉ፡፡

"ያ ማለት ግን ራሳቸውን መከላከል የሚችሉበት የተሻለ መንገድ የላቸውም ማለት አይደለም “በየቀኑ አዳዲስ” የጦር መሳሪያዎችን “እያገኙ ነው” ብለዋል፡፡

ባለፈው ሳምንት ዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬንን ጦር ለማጠናከር ከመደበችው 800 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ የተወሰነው ዩክሬን መግባቱ ተመልክቷል፡፡ የሉሃንስክ ገዥ በምስራቅ ዩክሬን የምትገኘው ክሬሚና ከተማ አሁን በሩሲያ ኃይሎች ቁጥጥር ስር ናት ብለዋል፡፡

ይህ ሩሲያ የዶናባስ መዲና ወደሆነቸው ክራማቶርስክ እንድታመራ ያስችላታል ተብሏል፡፡ ይሁን እንጂ ዩክሬን ሰባት የተለያዩ የሩሲያ ጥቃቶችን በተለያዩ ውጊያዎች በመልቀልበስ 10 ታንክችንና 18 ብረት ለበስ የጦር ክፍሎችን መደምሰሷን ትናገራለች፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቴር ሩሲያ በተለያዩ ወታደራዊ ዘርፎች የተዋቀሩ ወደ 11 የሚደርሱ ተጨማሪ ብርጌዶችና ክ8 እስከ 11ሺ የሚደርሱ አዳዲስ ወታደሮች ወደ ዩክሬን መላኳን አስታውቋል፡፡

ሁለቱን ከተሞች ሉሃንስክ እና ዶንቴስክን በሚያካትተው የዶናባስ ክፍለ ግዛት የተወሰነው ክፍል በደቡብ ያለቸው ማሪዮፑልን ጨምሮ በሩሲያ በሚደገፉ ተንገጣዮች የተያዘ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG