በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን ለቪቭ ከተማ በከባድ ሚሳዬል ተመታች


ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረሰችው ጥቃት በቀጠለበት፣ የወታደራዊ መሰረት ልማት ተቋማት ላይ የደረሰው ጉዳት በቪቭ፤ ዩክሬን ሚያዚያ 18/2022
ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረሰችው ጥቃት በቀጠለበት፣ የወታደራዊ መሰረት ልማት ተቋማት ላይ የደረሰው ጉዳት በቪቭ፤ ዩክሬን ሚያዚያ 18/2022

በምዕራብ ዩክሬን የሚገኙ ባለሥልጣናት ዛሬ ሰኞ በለቪቭ ከተማ ላይ በተካሄደ የሚሳዬል ጥቃት ቢያንስ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን አስታወቀዋል፡፡

የለቪቭ አገረ ገዥ ማክሲም ኮዝያስትኪ በሰጡት መግለጫ ሦስት ሚሳዬሎች የወታደራዊ መሰረት ልማት ተቋማትን የመቱ ሲሆን ሌላኛው ሚሳዬል የመኪና ጎማ መቀየሪያ ጋራዥ መምታቱን ተናግረዋል፡፡

በሌሎች ስፍራዎች ሰላማዊ ሰዎችን ከአካባቢው ለማውጣት ይደረጉ የነበሩ ጥረቶች ባላፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት መቋረጣቸው ተመልክቷል፡፡

የዩክሬን ምትክል ጠቅላይ ሚኒስትር አርያና ቨርሽቹክ፣ በማህበራዊ ሚዲያ ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት “ዓለም አቀፉን ህግ በመጣ የሩሲያ ወራሪዎች ሰላማዊ ሰዎች እንዳይወጡ ማገዱንና ሰብአዊ መውጫ መንገዶችን መደብደባቸው አላቋረጡም” ብለዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በስተደቡብ በምትገኘው ማሪዮፑል ትጥቃቸውን አውርደው እጃቸውን እንዲሰጡ ተከበው የሚገኙ ዩክሬናውያን፣ እጅ ላለመስጠት እየተዋጉ መሆኑን ጠቅሰው፣ የሩሲያ ኃይሎች የካርኪቭና አካባቢው የሚገኙ መኖሪያ ቤቶችን በሞርታርና ከባድ መሳሪያዎች በመደብደብ ሆን ብለው ሽብር እያራመዱ ነው ሲሉ ከሰዋቸዋል፡፡

ዘለንስኪ ትናንት እሁድ በሰጡት የቪዲዮ መግለጫ ሩሲያ በምስራቅ ዶናባስ ግዛት በቅርቡ ጥቃት መሰንዘር እንደምትጀምር አስታውቀዋል፡፡

ሩሲያ ኃይሎችዋን ከዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭና በሰሜን ከሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች በቅርብ ሳምንታት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ በማድረግ፣ በምስራቅ ዩክሬን መልሳ በማሰማራት ተጠናክራ ልትመጣ እንደምትችል የምዕራባውያን ወታደራዊ ባለሥልጣናት ገምተው እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ሉሃንስክ እና ዶንትስክን የሚጨምረውን የዶንባስ ግዛት በስተደቡብ ካለቸው የወደቢቷ ከተማ ማሪዮፕል ጋር ጨምሮ መያዝ፣ ሩሲያ እኤአ በ2014 ከያዘችው የክሪሚያ ሰርጥ ጋር መተላለፊያ የሆነውን የምድር መተላለፊያ አካባቢ ለመቆጣጠር እንደሚያስችላት ተነግሯል፡፡

ዘለንስኪ ባለፈው ዕሁድ በሲኤንኤን ላይ በተላለፈው ቃለ ምልልሳቸው ለዩክሬን የዶናባስ ውጊያ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ምክንያቱም ሩሲያ አካባቢውን ከተቆጣጠረችው ኪየቭን እንደገና ለመቆጣጠር መሞከሯ አይቀርም ብለዋል፡፡

ዘለነስኪ አክለውም “ይህን አካባቢ እንዲቆጣጣሩ አለመፈቅድ ለኛ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ጸንተን መቆም ይኖብናል ምክንያቱም ይህ ውጊያ ጠቅላላውን ውጊያ ይወስነዋል” ብለዋል፡፡

ሩሲያ ከተማውን የተቆጣጠረች መሆንዋን በመግለጽ በማሪዮፑል የቀሩትን የዩክሬን ተዋጊዎች እጃቸውን እንዲሰጡ ጠይቃለች፡፡

ከተማ ውስጥ የቀሩት 2ሺ500 ዩክሬናውያን ወታደሮች እና 400 ቅጥረኞች ኤዞቫስታል በተባለው የብረት ማምረቻ ውስጥ እንደሚገኙ ተመልክቷል፡፡ የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር ዴኒስ ሽሚሃል ትናንት ዕሁድ ለኤቢሲ ቴሌቪዥን በዚህ ሳምንት ፕሮግራም ላይ “የአገሪቱ ኃይሎች በማሪዮፑል እስከመጨረሻው ይዋጋሉ” ብለዋል፡፡

ሩሲያ እጅ እንዲሰጡ የሰጠችው የማስጠንቀቂያው ቀነ ገደብ ከተጠናቀቀ ሰዐታት በኋላ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት መግለጫ “ይህች ከተማ ገና አልወደቀችም” ብለዋል፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ሞስኮ ጦርነቱን ያሸነፈች መሆኑን ያምናሉ የተባለውን ሪፖርት አስመልከቶ የተጠየቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሽሚሃል ምንም እንኳ ብዙ ከተሞች በጥቃት ስር ቢሆኑም በደቡብ በሩሲያ ቁጥጥር የዋለችው ከተማ ከሄርሰን ብቻ መሆንዋን ገልጸዋል፡፡

“ከ900 በላይ ትላልቅና ትናንሽ ከተሞች እንዲሁም መንደሮች ከሩሲያ ነጻ ወራሪዎች ነጻ ወጥተዋል” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ዩክሬን በምስራቅ የምትገኘውን ዶናባስ ክፍለ ግዛትን አሳልፋ የመስጠት ሀሳብ የላትም ብለዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም “ከተቻለ” ዩክሬን የዲፕሎማሲ መፍትሄን ትሻለች ብለዋል፡፡

“አገራችንን ቤተሰባችንና መሬታችንን መተው አንፈልግም” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ዘለንስኪ እሁድ ምሽቱን በሰጡት መግለጫ የምዕራብ አገሮች የሩሲያን ነዳጅ እና የባንኩን ዘርፍ ጨምሮ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ መጣል አለባቸው ብለዋል፡፡

“እያንዳንዱ በአውሮፓና አሜሪካ የሚገኝ ሩሲያ ም ዕራባውያን አገሮችን ለማናጋት ነዳጅን እንደመሳሪያ እንደምትጠቀም ከወዲሁ በግልጽ አይቶታል” ብለዋል ዘለነስኪ፡፡

“ይህ ሁሉ የሚያሳየው ምዕራባውያን አገሮች አዳዲስ ማዕቀቦችን በፍጥነት መጣል ያለባቸው መሆኑን ነው" በማለትም ተናግረዋል፡፡

“ስፔይን ከዩክሬን ጋር ናት እኛ ከፑትን ተቃራኒ ነን” ያሉት የስፔይን ጠቅላይ ሚኒስትር ፔድሮ ሳንቼዝ፣ ዛሬ ሰኞ ከአንቴና 3 ቴሌቭዥን ጋር በሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ስፔይን በቅርቡ ኤምባሲዋን በኪየቭ ለመክፈት መወሰኗ ለዩክሬን ህዝብ ያላትን ድጋፍ ያመለክታል ብለዋል፡፡

የሩሲያ ወረራ በርካታ አገሮችን በኪየቭ ያላቸውን የዲፕሎማሲ ግንኙነት እንዲያቋርጡ ሲያደርጋቸው ብዙዎቹ ወደ ለቪቭ አዛውረዋል፡፡ ጣልያን ፈረንሳይ ቼክ ሪፕበሊክ በኪየቭ ያለውን ኤምባሲያቸው መልሰው የከፈቱ ወይም ለመክፈት ማሰባቸውን ከሚያስታውቁ አገሮች መካከል ናቸው፡፡

ሩሲያ የመጀመሪያ ዓለማዋ ዩክሬኒያውያንን ትጥቅ ማስፈታት በዚያ የሚገኙ ብሄራዊ አርበኞችን ማሸነፍ እንደነበር ገልጻለች፡፡ ኬየቭና ምዕራባዊ አጋሮችዋ ግን ያ ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን ይናገራሉ፡፡

44 ሚሊዮን ህዝብ ላይ ያለበቂ ምክንያት የተከፈተው ጦርነት አንድ አራተኛ የሚሆነውን ህዝብ ከቤት ንብረቱ እንዲፈናቀል ያደረገ መሆኑን ይገልጻሉ፡፡

XS
SM
MD
LG