በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በዩክሬን ለተሰራው ግፍ ፑቲን በጦር ወንጀል እንዲከሰሱ ጠየቁ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ዛሬ ሰኞ በሰጡት መግለጫ የሩሲያ ወታደሮች በቀናት ውስጥ ሲዘገብ እንደቆየው በዩክሬን አድርሰዋቸዋል የተባሉትን ጥቃቶች ያወገዙ ሲሆን በዩክሬን መዲና አቅራቢያ በምትገኘው ቡቻ ተፈጽሟል ለተባለው ጥቃት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑትን በጦር ወንጀለኝነት መከሰስ አለባቸው ብለዋል፡፡

ባይደን በዋይት ሀውስ ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ “ፕሬዚዳን ፑቲንን የጦር ወንጀለኛ አድርጌ በመጥራቴ ስተች እንደነበር ታስውስላችሁ ስለዚህ እውነተኛውን ነገር ተመለከታችሁ፡፡ በቡቻ የሆነውን አይታችኋል፡፡ ይህ መግለጫ ...የጦር ወንጀለኛ ናቸው፡፡ ግን መረጃዎችን ማሰባሰብ ይኖርብናል፡፡” ብለዋል፡፡

ባይደን አያይዘው “እኚህ ሰው (ፑቲን) ጨካኝ ናቸው፡፡ በቡቻ የሆነው ነገር እጅግ የሚያስቆጣ ነው፡፡ ደግሞም ሁሉም ሰው ያየ ነው” ብለዋል፡፡

ባይደን የሳምንቱን የእረፍት ጊዚያቸውን ካሳስለፉበት መኖሪያቸው ከሆነው ደለዌር ወደ ዋሽግንተን ሲመለሱ “ተጨማሪ ማዕቀብ መጣሉን እቀጥላለሁ” ብለዋል፡፡

በኪየቭ አካባቢ ከሚገኙና ሩሲያውያኑ በቅርቡ ለቀዋቸው ከወጡባቸው አካባቢዎች 410 የሚሆኑ ሲቪሎች አስክሬን የተነሳ መሆኑን የዩክሬን ጠቅላይ አቃቤ ህግ ኢርያና ቨነዲክቶቫ ተናግረዋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት ኮሚሽነር ኡርሱላ ቮንደር ሌን ዛሬ ሰኞ ባስተላለፉ የትዊት መል ዕክት የአውሮፓ ህብረት መርማሪዎችን ወደ ዩክሬን በመላክ ዩክሬናውያኑ የጦር ወንጀሎችን በዝርዝር እንዲመዘግቡ የሚያግዟቸው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ በጦርነቱ የተጎዳችውን ቡቻ ከተማን ዛሬ የጎበኙ ሲሆን በአገሪቱ ቴሌቪዥን ለህዝባቸው በሰጡት መግለጫ የሞስኮ ወታደሮች የፈጸሙት ግፍ ገሀድ በሆነበት በዚህ ሁኔታው ውስጥ አሁን ከሩሲያ ጋር ጦርነቱን እንዲቆም ለመደራደር እጅግ ከባድ ነው ብለዋል፡፡

XS
SM
MD
LG