በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ ለመጣል በአስቸኳይ ይሰበሰባል


የጅምላ መቃብር ከዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ በስተሰሜን ምዕራብ በቡቻ እአአ ሚያዚያ 3/2022
የጅምላ መቃብር ከዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ በስተሰሜን ምዕራብ በቡቻ እአአ ሚያዚያ 3/2022

ዩክሬን ውስጥ የሚገኙ የሩሲያ ኃይሎች፣ በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ፈጽመውታል የተባለውን የሰብአዊ ጥቃት ሪፖርት ተከትሎ፣ የአውሮፓ ህብረት፣ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ በሚጣልበት ሁኔታ ላይ ለመምከር እንደሚሰበሰብ፣ ዛሬ ሰኞ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ጆሴፍ ቦሬል በሰጡት መግለጫ “ህብረቱ ጉዳዩን እንደ አጣዳፊ ጉዳይ በመውሰድ በሩሲያ ላይ ተጨማሪ ማዕቀብ በሚጣልበት ሁኔታ ላይ ይሠራል” ብለዋል።

ቦሬል “በቡቻ እና በሌሎች የዩክሬን ከተሞች ላይ የተፈጸመው እልቂት በአውሮፓ ምድር ከተፈጸሙት ግፎች ሁሉ እጅግ የሚደንቅ ነው” ብለዋል፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ትናንት እሁድ በሲኤንኤን ቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ በሰጡት መግለጫ፣ የሩሲያ ወታደሮች አካባቢውን ትተው ከሄዱ በኋላ በኪየቭ አቅራቢያ ባለቸው የየቡቻ ከተማ በየጎዳናው ተጥሎ የሚታዩትና ለመላው ዓለም ይፋ የተደረገውን የዩክሬናውያን አስክሬን በመጥቀስ በሩሲያ ላይ ከፍተኛ ወቀሳ ሰንዝረዋል፡፡

“ምንም ማድረግ አትችልም ዝም ብሎ አንጀነትን ያቆስልሃል፡፡” ያሉት ብሊንከን “ይሁን እንጂ ይህን ጉዳይ ዝምብለን ልንመልከተው አንችልም፡፡ የተለመደ ተራ ነገር እንዲሆን ማድረግ አንችልም፡፡” ብለዋል፡፡ ብሊንከን በዚህ ሳምንት ከሌሎች የኔቶ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር ሩሲያ ለፈጸመቸው ተግባር ተጠያቂ በምትሆንበት ሁኔታ ላይ ለመምከር ወደ ብራስልስ እንደሚያመሩ ተገልጿል፡፡

የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጆን ስቶልተንበርግም እንዲሁ ሲኤንኤን ላይ ቀርበው ሲናገሩ

“በአስርት አመታት ያላየነው በሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸ ጭካኔ ነው” ካሉ በኋላ ይህን ጦርነት እንዲያበቃ ማድረግ የፕሬዚዳንት ፑቲን ኃላፊነት ነው ብለዋል፡፡ ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተመልካች ወይም የሂዩማን ራይትስ ዎች የአውሮፓና የመከካለኛው እስያ ድሬክተር በበኩላቸው

“እየመዘግብነው ያለው ቃል አይገኝለትም፣ ሆን ተብሎ በዩክሬን ሲቪሎች ላይ የሚፈጸም የጭካኔ ተግባር ነው” ብለዋል፡፡ ዳይሬክተሩ በሩሲያ ኃዩሎች “አስገድዶ መድፈር ግድያ እና በሩሲያ ኃይሎች ቁጥጥር ስር በነበሩ ሰላማዊ ሰዎች ላይ የተፈጸሙ ሌሎች ጥቃቶች በጦር ወንጀለኝነት ሊመረመሩ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ይደረግ በነበረው ዓመታዊ የሙዘቀኞች የሽልማት ወይም ግራሚ አዋርድ ላይ በድንግት የቀረቡት የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ንግግር አስምተዋል፡፡

“ከዝምታ በቀር በምትችሉት ሁሉ እርዱን” ያሉት ዘለነስኪ “የኛ ሙዚቀኞች ከሙሉ የሱፍ ልብስ ወይም ተክሲዶ ይልቅ የጦር ልብስ ለብሰዋል፡፡ በሆስፒታሎች ለሚገኙ ቁስለኞች እየዘፈኑ ነው ምንም እንኳ አንዳንዶቹ ባይሰሟቸውም” ብለዋል፡፡

የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር እሁድ ባወጣው መግለጫ በቡቻ ሰላማዊ ሰዎች አለመግደሉን ገልጾ በቪዲዮ የተቀረበውን የአስክሬን ምስልና ቪዲዮዎችን ሌላኛው የምዕራባውያን ትንኮሳ ነው ብለውታል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ በዩክሬን ቡቻ ላይ በተፈጸመው ጉዳይ እንደሚነጋገር ተዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG