በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካምላ ሃሪስ ሩስያ በዩክሬን “የፈጸመችው” የጦር ወንጀል እንዲመረመር በሚል የቀረበውን ጥሪ ደገፉ


የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ
የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ

የዩናይትድ ስቴትሷ ምክትል ፕሬዚዳንት ካማላ ሃሪስ በዩክሬይን ህጻናት እና ነፍሰ ጡር እናቶች በነበሩበት የወሊድ አገልግሎት መስጫ ሆስፒታል ላይ ደረሰ የተባለውን የቦምብ ጥቃት ጨምሮ፣ ሩሲያ በዩክሬኑ ወረራ ፈጽማለች የተባለው “ዓለም አቀፍ የጦር ወንጀል እንዲመረመር” ሲሉ የዓለም መሪዎች ዛሬ ሃሙስ ላሰሙት ጥሪ ድጋፋቸውን ሰጡ።

ሃሪስ በዋርሶ አገራቸው በምስራቅ አውሮፓ ላሉ የኔቶ አጋሮቿ የምትሰጠውን ድጋፍ ለማሳየት ከፖላንዱ ፕሬዚዳንት አንድሬ ዱዳ ጋር ተገናኝተው ከመወያየታቸው አስቀድሞ በሰጡት አስተያየት የተባለውን ምርመራ አስፈላጊነት አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

ይህ የምክትል ፕሬዚዳንት ሃሪስ “የሩስያ ድርጊት ይመርመር” የሚለው ጥሪ የተሰማው የዩክሬን ባለሥልጣናት እንዳሉት የሩስያ የዓየር ድብደባ በዩክሬኗ የማሪፑል ከተማ በሚገኝ አንድ የእናቶች ሕክምና መስጫ ሆስፒታል ላይ በደረሰ ጉዳት አንድ ህጻን ጨምሮ ለሦስት ሰዎች ህይወት መጥፋት ምክንያት መሆኑ በተዘገበ ማግስት ነው።

"ዩክሬን ውስጥ ሩሲያውያን የጦር ወንጀሎችን እየፈጸሙ መሆኑ ለእኛ ግልጽ ነው፤ "ካሉት ከሆላንዱ ፕሬዚዳንት ዱዳ ጎን የቆሙት ሃሪስ ጉዳዩ "ያለጥርጥር መርመር አለበት። እናም ሁላችንም ልንመለከተው ይገባል" ብለዋል።

ሃሪስ በመግለጫቸው ወቅት ሩሲያ በዩክሬን ላይ ባካሄደችው “ፍትሃዊ ያልሆነ” ባሉት ወረራ የተጎዱ ንጹሃን ዜጎችን ለመደገፍ አገራቸው የምትሰጠውን አዲስ የ53 ሚሊዮን ዶላር የሰብዓዊ ዕርዳታም ይፋ አድርገዋል።

ከሁለት ሳምንታት በፊት ዩናይትድ ስቴትስ ለህክምና ቁሳቁሶች፣ ለምግብ፣ ለሙቀት ሰጭ አልባሳት እንዲሁም ለሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች የሚውል 54 ሚሊዮን ዶላር መለገሷም ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG