በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ የዩክሬን ግዛቶችን ወደ ራሷ የቀላቀለችበት ቀን አከበረች

The Moscow-appointed heads of Ukraine's Kherson region and Donetsk and Lugansk separatist leaders join hands with Russian President Vladimir Putin (center) after signing treaties annexing four regions of Ukraine Russian troops occupy, in Moscow on Sept. 3

ሩሲያ አራት የዩክሬን ግዛቶችን ወደ ወደ ራሷ የቀላቀለችበትን ሥነ ሥርዓት ለማክበር በተዘጋጀችበት ዕለት በዛፕሮዥዚያ እና ማይኮሊቭ የሚገኙ ከተሞች አቅራቢያ የተፋናቃይ ቤተሰቦችን ጭነው በአጀብ ይጓዙ በነበሩ የሰብአዊ አገልግሎት ሰጭ ተሽከርካሪዎችን የሩሲያ መድፎች መደብደባቸው ተነገረ፡፡

በዛፕሮዝዢያው ድብደባ ቢያንስ 23 ሰዎች ሲሞቱ 28 የሚሆኑት ደግሞ መቁሰላቸውን እንዲሁም በማይኮሊቭ ሦስት ሰዎች ተገድለው 12 መቁሰላቸው ተነገሯል፡፡

የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን አራቱን ዩክሬን ግዛቶች ዶነቴስክ፣ ሉሃንስክ፣ ከኻርሰንና ዛፕሮዥዢያን ዛሬ ዓርብ ወደ ራሳቸው ግዛት የሚቀላቀሉበትንና ብዙዎቹ ህገወጥ እምርጃ አድርገው ሊመለከቱት የሚችለውን ሰነድ እንደሚፈርሙ ተገልጿል፡፡

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዜለነስኪ ስለጉዳዩ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ባለሥልጣኖቻቸውን ትናንት ሀሙስ አስቸኳይ ስብሰባ ጠርተው እንደነበር ሲነገር የዩክሬን ብሄራዊ የፀጥታና መከላከያ ም/ቤትም ዛሬ ዓርብ እንደሚሰበሰብ ተመልከቷል፡፡

XS
SM
MD
LG