በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ በጥቁር ባህር ኦዴሳ ወደብ አቅራቢያ የሚገኘውን "ስኔክ አይላንድ" ደሴት ለቀቀች


ይህ ምስል ማክሰር ቴክኖሎጂ "ስኔክ አይላንድ" የተባለው የጥቁር ባህር ደሴት ያሳያል፤ እአአ ሰኔ 30/2022
ይህ ምስል ማክሰር ቴክኖሎጂ "ስኔክ አይላንድ" የተባለው የጥቁር ባህር ደሴት ያሳያል፤ እአአ ሰኔ 30/2022

የሩሲያ የመከላከያ ሚኒስቴር "ስኔክ አይላንድ" የተባለውን የጥቁር ባህር ደሴት ለቅቀናል ሲል አስታወቀ።

ሩሲያ ባለፈው የካቲት ዩክሬን ላይ ጦርነቱን በከፈተችበት ወቅት ደሴቲቱን ይዛ ለጥቃቷ መንደርደሪያ አድርጋ ስትጠቀምባት ቆይታለች።

ሩሲያ ደሴቲቱን መልቀቋን ያስታወቀችው የዩክሬን ኃይሎች በዚያ ያላትን ይዞታዎች መደብደባቸው ተከትሎ መሆኑ ታውቋል።

ሩሲያ በሰጠችው መግለጫ ደሴቷን የለቀቅኩት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከዩክሬን የእህል ምርት የሚወጣበት መስመር ለመክፈት የሚያደርገውን ጥረት የማደናቀፍ ፍላጎት እንደሌለን ለማሳየት ነው ብላለች።

የዩክሬን መንግሥትም ሩሲያ ደሴቷን መልቀቋን አረጋግጦ የወጡት የጦር ሰራዊታችን በወሰደው የተሳካ ዕርምጃ ምክንያት ነው ብሏል።

በሌላ ዜና ብሪታኒያ ለዩክሬን የአንድ ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ ዕርዳታ እንደምትሰጥ ገልጻለች። የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜሌንስኪ ብሪታንያን ዕውነተኛ ወዳጅ እና የስትራተጂ አጋር በማለት አመስግነዋል።

XS
SM
MD
LG