በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኮምሽን ለዩክሬን የአውሮፓ ህብረት ዕጩነት ኮሚሽን ድጋፉን ሰጠ


የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ፣ የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑዌል ማክሮን ከኪየቭ በተጨማሪ ኢርፒን ጎብኝተዋል እአአ ሰኔ 16/2022
የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ፣ የፈረንሳይ ፕሬዚደንት ኢማኑዌል ማክሮን ከኪየቭ በተጨማሪ ኢርፒን ጎብኝተዋል እአአ ሰኔ 16/2022

ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት አባልነት ዕጩ እንድትሆን የአውሮፓ ኮሚሽን ድጋፉን ሰጠ።

የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሱላ ቮን ደር ሌዬን ዛሬ ብረሰልስ ላይ በሰጡት ቃል "ዩክሬናውያን ለአውሮፓ አመለካከት የሚሞቱ መሆናቸውን ሁላችንም እናውቃለን። ስለዚህም ከኛ ጋር የአውሮፓን ህልም እየተቋደሱ አብረውን እንዲኖሩ እንፈልጋለን" ብለዋል።

ይህ ዩክሬን ዕጩ እንድትሆን ይፈቀድላት የሚለው ምክረ ሃሳብ የህብረቱ አባል ለመሆን መጓዝ ያለባት የረጅሙ ሂደት የመጀመሪያ ምዕራፍ የህብረቱ አባል ሀገሮች መሪዎች በቅርቡ ስብሰባ አድርገው በምክረ ሀሳቡ ዙሪያ ይነጋገራሉ። ኮሚሽኑ ሞልዶቫም የህብረቱ ዕጩ አባል እንድትሆን የደገፈ ሲሆን የጆርጂያን ዕጩነት ግን አልደገፈም።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭ የጎበኙት የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ኢማኑዌል ማክሮን የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ማሪዮ ድራጊ እና የሮሜንያ ፕሬዚዳንት ክላውስ ጆሃኒስ ከዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዘለንስኪ ጋር ተገንኝተው ተነጋግረዋል። ከውይይታቸው በኃላ በሰጡት ቃልም ዩክሬን የአውሮፓ ህብረት ዕጩነት እንደምታገኝ ፍንጭ ሰጥተዋል። የጀርመን ቻንስለር ኦላፍ "የመጣነው ግልጽ መልዕክት ይዘን ነው፤ ዩክሬን የአውሮፓ ቤተሰብ አባል ነች" ብለዋል።

የቀድሞ የሩሲያ ፕሬዚዳንት የነበሩት እና አሁን የክሬምሊን ቤተ መንግሥት የጸጥታ ምክር ቤት ምክትል ኃላፊው ዲሚትሪ ሜድቬዲየቭ የመሪዎቹ ጉብኝት፣

"ፋይዳ የለውም ዩክሬንን ወደሰላም አያቀርባትም። ይልቁኑ ጊዜው እያለፈ ነው" ብለዋል።

ዘለንስኪ በበኩላቸው የጦርነቱን ማብቃትም የሰላማችንንም ጉዳይ እኛ እንደምናውቅ መሪዎቹ መስማማታቸውን መስማቴ ትልቅ ነገር ነው ብለዋል።

ጦርነቱን ማሸነፋችን የሚወስነው ምዕራባውያን የምናገኘው የጦር መሳሪያ ድጋፍ መቀጠል ነው ብለዋል። ዩናይትድ ስቴትስ የአንድ ቢሊዮን ዶላር ተጨማሪ ወታደራዊ እርዳታ እንደምትሰጥ አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG