በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኪየቭ ከንቲባ “ዩክሬን በዓለም የነጻነት ቁልፍ ናት” አሉ


የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊትስችኮ በስዊዘርላንድ ዶቫስ ላይ በመካሄድ በሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚ ፎርም
የኪየቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊትስችኮ በስዊዘርላንድ ዶቫስ ላይ በመካሄድ በሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚ ፎርም

“ዩክሬን በዓለም የነፃነት ቁልፍ ናት” ያሉት በዩክሬን የኪየቭ ከንቲባ፣ ዓለም ትርጉም የለሽ ከሆነው የሩሲያ ጦርነት እንዲታደጋቸው፣ ስዊዘርላንድ ዶቫስ ላይ በመካሄድ በሚገኘው የዓለም ኢኮኖሚ ፎርም ላይ ዛሬ ሀሙስ ባሰሙት ንግግር አሳሰቡ፡፡

ከንቲባው ቪታሊ ክሊትስችኮ “ዩክሬን ማንንም የማትነካ “ሰላማዊ አገር ናት” ያሉ ሲሆን ዩክሬናውያን የአውሮፓውያን ቤተሰብ አካል መሆን ይፈልጋሉ” ብለዋል፡፡

“የሩሲያ መንግሥት የሶቭየት ሕብረትን ዳግመኛ የሚፈልግ በመሆኑ ዩክሬንን በመጠቅለል ብቻ አይቆምም” ሲሉም ተናግረዋል፡፡

ቪታሊ በንግግራቸው “እኛ እየተከላከልን ያለነው ቤተሰባችንና ልጆቻችንን ብቻ አይደለም፡፡ እኛ እናንተን እየተከላከልን ነው፡፡ ምክንያቱም አንድ ዓይነት እሴቶች ነው ያለን” ብለዋል፡፡

ዩክሬንን በፖለቲካና በኢኮኖሚ የደገፏቸውን፣ ተጨማሪ መሳሪያዎችን የላኩላቸውንና፣ ዩክሬናውያን ስደተኞችን የተቀበሉላቸውን አገሮች፣ ከንቲባው ባሰሙት ንግግር አመሰግነዋል፡፡

XS
SM
MD
LG