በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዘለንስኪ ለንግግሩ ብቸኛው መንገድ ከፑቲን ጋር የሚደረገው የቀጥታ ንግግር ነው አሉ


ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ
ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ከሩሲያ ጋር ለመደራደር ፈቃደኛ መሆናቸውን ገልጸው ይሁን እንጂ ይህን የሚያደርጉት "በቀጥታ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር ከሆነ ብቻ ነው" ሲሉ ዛሬ ረቡዕ ተናግረዋል፡፡

ለዓለም ኢኮኖሚ ፎረም ተሳታፊዎች ዛሬ ባሰሙት የቪዲዮ ንግግር ፑቲን እውነታውን የሚገነዘቡ ከሆነ ከዚህ ግጭት ለመውጣት የሚያስችል የዲፕሎማቲክ መንገድ አለ ብለዋል፡፡

ዘለንስኪ አክለውም፣ ከሩሲያ ጋር ለመነጋገር የመጀመሪያው እርምጃ የሚሆነው የሩሲያ ኃይሎች ባላፈው የካቲት ማብቂያ ላይ ዩክሬንን ከመውረራቸው በፊት፣ ወደነበሩበት ይዞታ መመለስ አለባቸው ብለዋል፡፡

በቅርብ ጊዜ ውስጥ ያሉ ሁኔታዎች ግን ወደ ንግግር የሚያመሩና ግጭቱንም በአጭር ጊዜ ውስጥ የሚያስቆሙ አለመሆናቸው ተመልክቷል፡፡

ዘለንስኪ በትናንትናው እለት በዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ውስጥ ባለ አንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በተደረገው የጅምላ ግድያ፣ ልጆቻቸው ለተገደሉባቸው ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል፡፡

ዘለንስኪ “እኔ እስከማውቀው ድረስ፣ 19 ህጻናትን ጨምሮ 21 ሰዎች ተገድለዋል፡፡ ሰላም ባለበት ሁኔታ ውስጥ የጅምላ ገዳዮችን ሰላባ ማየት አሰቃቂ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

የሩሲያ ሃይሎች በሉሃንስ ክፍለ ግዛት የሚገኘውን ሰቨሮዳነትስክን ጨምሮ፣ ምስራቃዊ ዩክሬንን እየደበደብ ባሉበት ሰዓት፣ የዘለንስኪ አማካሪ ማይክሂሎ ፖዶልያክ፣ የውጭ መንግሥታት፣ ሩሲያ በዩክሬን ውስጥ የምታደርገው ውጊያ እንዲያበቃ ግፊት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

ፖዶልያክ ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት “ዛሬ የወደፊቱ አውሮፓ በብራስል ወይም ዳቮስ ላይ አይመሰረትም፡፡ በሴቨሮዳንትስ እና ባክሙት አቅራቢያ ባሉ ምሽጎች ነው፡፡ የዚህ ጦርነት እድሜ የሚወሰነው የነዳጅ ማዕቀቡ በሚጣልበት እና የጦር መሳሪያው እርዳታ በሚቀርብበት ፍጥነት ነው፡፡ ይህ ጦርነት እንዲቆም ትፈልጋላችሁ? የሰላሙ ቁልፍ ያለው በእናነት እጅ ነው” ብለዋል፡፡

ይህ ዘለንስኪ ባለፈው ማክሰኞ ምሽት “ወደ ዩክሬን የሚላኩ ቦምብ ተሸካሚ ሮኬቶች፣ ታንኮች፣ የጸረ ባህር ኃይል ሚሳኤሎች፣ እና ሌሎች የጦር መሳሪያዎችን መላክ የሩሲያውን የወደፊት ጠብ አጫሪነት ለማስቆም ጥሩ ኢንቨስትመንት ነው ሲሉ ከተናገሩት ጋር የሚመሳሰል ነው፡፡

የምጣኔ ሀብት ግፊቶች

ዩናይትድ ስቴትስ ዛሬ ረቡዕ ጀምሮ የሚያበቃውን ሩሲያ ለዓለም አቀፍ ኢንቨርስተሮች እዳዋን የምትከፍለበት ጊዜ እንዲራዘም የማትፈቅድ መሆኑን አስታውቃለች፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ግምጃ ቤት ሩሲያ የዩናይትድ ስቴትስ ባንኮችን ተጠቅማ ክፍያዎችዋን እንድትከፍል ፈቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ያ መደረጉ ሥርዓት ያለው ሽግግር ለማስቻል ሲባል ኢንቨስተሮች ድርሻዎቻቸውን እንዲሸጡ ለማድረግ በጊዚያዊነት የተሰጠ ጊዜ እንደነበር ተመልክቷል፡፡

ያንን መንገድ መዝጋት ሩሲያ እዳዋን መክፈል የማትችልበትን መንገድ ከፍ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡

የኔቶ መስፋፋት

ከስዊድን እና ከፊላንድ የተውጣጡ መልዕክተኞች ሁለቱ አገሮች የኔቶ አባል ለመሆን ያቀረቡትን ማመልክቻ ወደ ተቃወመችው ቱርክ በማምራት ከባለሥልጣኖቹ ጋር ለመነጋገር ዛሬ ረቡዕ ቱርክ መዲና አንካራ መግባታቸው ተነግሯል፡፡

ቱርክ ስዊድንና ፊላንድ የኩርዲስታን ሠራተኞች ፓርቲ (ፒኬኬ) ተዋጊ ሚሊሽ ቡድኖችንና እኤአ በ2016 የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግሥት አቀነባብረዋል ያለቻቸውንና መሰረታቸውን ዩናይትድ ስቴትስ ያደረጉ የእስልምና ሀይማኖት መሪ ፈተፉላ ጉሌንን ይደግፋሉ ስትል ከሳለች፡፡

ለኔቶ አባልነት የሚቀርበው ጥያቄ በአሁኑ ወቅት አባል የሆኑትን የሁሉንም አገሮች ይሁንታ የሚጠይቅ ነው፡፡ የኔቶ ዋን ጸሀፊ ጄኔራል ጄን ስቶልተንበርግ የትኛውም ተቃውሞን ተቋቅዩሞ ስዊድንና ፊላንድን ወደ ጥምረቱ ለመቀላቀል እንደሚቻል ባለሙሉ ተስፋ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

XS
SM
MD
LG