በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን ተጨማሪ ወታደራዊ እርዳታ በማዘጋጀት ላይ ነች


ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

ዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሩሲያ ዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጥቃት የዘር ማጥፋት ብለው አውግዘዋል። የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቪላዲሚር ፑቲን በበኩላቸው የተከበረውን ግባችንን ለማሳካት መዋጋታችንን እንቀጥላለን ብለው ዝተዋል።

የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ሩሲያን ድል ለመምታት ተጨማሪ እርዳታ እየተማጸኑ ሲሆን ዩናይትድ ስቴትስ ለፀጥታ ድጋፍ የሚውል ተጨማሪ ሰባት መቶ ሃምሳ ሚሊዮን ዶላር እንደምትሰጥ በቅርብ ጊዜ ይፋ ታደርጋለች ተብሎ ይጠበቃል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን እና የብሪታንያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ሩስያ ግፍ ለምትፈጽምባት ለዩክሪን የፀጥታ እና ሰብዓዊ እርዳታ መስጠታችንን እንቀጥላለን በማለት ትናንት በድጋሚ ቃል መግባታቸውን ዋይት ኃውስ አስታውቋል።

ፕሬዚዳንት ባይደን የሩሲያውን ፕሬዚዳንት ዩክሬን ላይ የዘር ማጥፋት ዘመቻ እየመሩ ነው ሲሉ አጥብቀው አውግዘዋል። ባይደን ቡቻ ላይ ስለተፈጸመው ግፍ ማሰረጃ መገኘቱን ተከትሎ ፑቲንን ለፍርድ መቅረብ ያለባቸው የጦር ወንጀለኛ በማለት ደጋግመው ኮንነዋቸዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስቲር ዩክሬን ስለሚያስፈልጋት የጦር መሳሪያ ለመነጋገር ከትላልቆቹ የመከላከያ ሥራ ተቁዋራጭ ኩባኒያዎች ጋር ዛሬ በዝግ ስብሰባ እያካሄደ ነው።

XS
SM
MD
LG