በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ለዩክሬን ደህንነት የ800ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ይፋ አደረጉ

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መንግስታቸው ዩክሬን ከሩሲያ ወረራ ራሷን መከላከል እንድትችል ለመርዳት የ800 ሚሊዮን ዶላር የደህንነት እርዳታ ለማድረግ መወሰኑን ባስታወቁበት ወቅት ፣ ዋይት ሀውስ እኤአ የካቲት 16 2022

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን መንግስታቸው ዩክሬን ከሩሲያ ወረራ ራሷን መከላከል እንድትችል ለመርዳት ባለፈው ሳምንት ከመደበው የ200 ሚሊዮን ዶላር በተጨማሪ የ800 ሚሊዮን ዶላር የደህንነት እርዳታ ለማድረግ መወሰኑን አስታውቀዋል፡፡

ይህ የተገለጸው የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ፣ ትናንት ረቡዕ፣ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት ያደረጉትን ንግግር ተከትሎ ነው፡፡

በሩሲያና በዩክሬን ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ በኪየቭ፣ ማሪዮፖሎና በሌሎች የዩክሬን ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሎሏል፡፡ የሩሲያ ኃይሎች ስለሚያደርሱት ጥቃት ፕሬዚዳንት ባይደን

“ፑቲን በዩክሬን ላይ አሰቃቂ ጥፋትና ውድመት እየፈጸሙ ነው፡፡ የአፓርትመንት ህንጻዎችን፣ የማዋለጃ ሥፍራዎችንና ሆስፒታሎችን በቦምብ እየደበደቡ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳን ጆ ባይደን መንግስታቸው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ይፋ ካደረገው የ200 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ በተጨማሪ የ800 ሚሊዮን ዶላር የደህንነት እርዳታ ለማድረግ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህ ባለፈው ሳምንት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ካሳለፋቸው የ13.6 ቢሊዮን ዶላር ዘርፈ ብዙ የበጀት ውሳኔዎች መካከል የሚመደብ ነው፡፡

800 ሚሊዮን ዶላሩ በቀጥታ የአየር መከላከያ መሳሪያዎችን ጨምሮ ጸረ ሚሳዬሎች፣ የጦር ድሮኖችና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችና ቦምቦችን ለመሳሰሉት መሳሪያዎች መግዣ የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ባይደን ለዩክሬን ደህንነት የ800ሚሊዮን ዶላር እርዳታ ይፋ አደረጉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:29 0:00

የዊልሰን ሴንተር ተቋም አማካሪ ምክርቤት ሊቀመበር ማይክ ኪማጅ እንዲህ ይላሉ

“እንደውነቱ ከሆነ ሩሲውያውንን ሊያቆማቸው የሚችለውና በወታደራዊ አቅማቸው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ሊያስከትሉ የሚችሉት የጸረ አውሮፕላን ወይም የአየር መከላከያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ዋነኛው ታክቲካል ስትራቴጂ ትኩረት ያረፈው በነዚህ የጦር መሳሪያዎች ላይ መሆኑ ለዚህ ነው፡፡”

ትናንት ረቡዕ ማለዳው ላይ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ለዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባላት በቀጥታ ባሳሙት የቪዲዮ ንግግር ፤የምክር ቤቱ አባላትንና ፕሬዚዳንት ባይደንን እንዲህ ሲሉ ተማጽነዋል፡፡

“እናንተ የዓለም መሪ እንድትሆኑ እመኛለሁ፡፡ የዓለም መሪ ማለት የሰላም መሪ መሆን ማለት ነው፡፡”

ምንም እንኳ ዘለንስኪ የአየር ቀጠናው ነጻ እንዲሆን የተማጸኑ ቢሆንም ዩናይትድ ስቴትስ ግን ይህን በመደገፍ ሁኔታዎችን ለማመቻቸትም ሆነ ጀቶችን ለመላክ ፈቃደኛ አይደለችም፡፡

በውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ምክር ቤት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ስቴፈን ቢድል እንዲህ ይላሉ

“ዩክሬናውያኑ ትልቅ ስጋት የሆነባቸው የተለመደው መድፍ መደበኛው ሚሳዬልና መደበኛው እግረኛ ጦር ነው፡፡ የአየር ክልል ላይ እንዳይጣስ የበረራ እቀባ መጣሉ የዚያን ያህል ምንም ተጽዕኖ አይኖረውም፡፡ ስለዚህ በምድር ላይ ያለውን ወታደራዊ ግጭት እንዲባባስ ምክንያት በመሆን የበለጠ አደጋ ይፈጥራል፡፡ የፖላንድን ተዋጊ ጀቶች ወደ ዩክሬናውያኑ ማስተላለፍም ተመሳሳይ ውጤት ነው የሚኖረው፡፡

ትናንት ረቡዕ የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር ሎይድ ኦስተንን ጨምሮ የኔቶ መከላከያ ኃላፊዎች ብራስልስ ውስጥ ተሰብሰበዋል፡፡

ሞስኮ ጥቃቷን የኔቶ አባል ወደሆኑት አገሮችም ልታስፋፋ ትችላለች የሚል ስጋት በመኖሩ አባል አገሮቹ ተሰብስበው የሩሲያን እርምጃ ማቆም የሚችሉበትን አዳዲስ እቅዶች መንደፍ እንደሚገባቸው የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጀኔራል ስቶልትንበርግ

“ሁሉንም አጋሮቻችንን ለመከላከል ዝግጁ መሆናችንን በማስረዳት ሞስኮ ያላትን የተሳሳተ ስሌት እንድትረዳ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በምክር ቤቱ ከጸደቀው የ13.6 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 4 ቢሊዮን ዶላሩ በጦርነቱ ሳቢያ ከዩክሬን ለተፈናቀሉት ወደ 3 ሚሊዮን ለሚጠጉ ሰዎች ሰብአዊ እርዳታ የሚውል መሆኑ ተመልክቷል፡፡

በሩሲያና በዩክሬን ኃይሎች መካከል የሚደረገው ውጊያ በኪየቭ፣ ማሪዮፖሎና በሌሎች የዩክሬን ከተሞች ተጠናክሮ ቀጥሎሏል፡፡ የሩሲያ ኃይሎች ስለሚያደርሱት ጥቃት ፕሬዚዳንት ባይደን

“ፑቲን በዩክሬን ላይ አሰቃቂ ጥፋትና ውድመት እየፈጸሙ ነው፡፡ የአፓርትመንት ህንጻዎችን፣ የማዋለጃ ሥፍራዎችንና ሆስፒታሎችን በቦምብ እየደበደቡ ነው፡፡” ብለዋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳን ጆ ባይደን መንግስታቸው ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ ይፋ ካደረገው የ200 ሚሊዮን ዶላር እርዳታ በተጨማሪ የ800 ሚሊዮን ዶላር የደህንነት እርዳታ ለማድረግ መወሰናቸውን አስታውቀዋል፡፡

ይህ ባለፈው ሳምንት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት ካሳለፋቸው የ13.6 ቢሊዮን ዶላር ዘርፈ ብዙ የበጀት ውሳኔዎች መካከል የሚመደብ ነው፡፡

800 ሚሊዮን ዶላሩ በቀጥታ የአየር መከላከያ መሳሪያዎችን ጨምሮ ጸረ ሚሳዬሎች፣ የጦር ድሮኖችና የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችና ቦምቦችን ለመሳሰሉት መሳሪያዎች መግዣ የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የዊልሰን ሴንተር ተቋም አማካሪ ምክርቤት ሊቀመበር ማይክ ኪማጅ እንዲህ ይላሉ

“እንደውነቱ ከሆነ ሩሲውያውንን ሊያቆማቸው የሚችለውና በወታደራዊ አቅማቸው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ሊያስከትሉ የሚችሉት የጸረ አውሮፕላን ወይም የአየር መከላከያ መሳሪያዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ ዋነኛው ታክቲካል ስትራቴጂ ትኩረት ያረፈው በነዚህ የጦር መሳሪያዎች ላይ መሆኑ ለዚህ ነው፡፡”

ትናንት ረቡዕ ማለዳው ላይ የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮሎድሚር ዘለንስኪ ለዩናይትድ ስቴትስ የምክር ቤት አባላት በቀጥታ ባሳሙት የቪዲዮ ንግግር፤ የምክር ቤቱ አባላትንና ፕሬዚዳንት ባይደንን እንዲህ ሲሉ ተማጽነዋል፡፡

“እናንተ የዓለም መሪ እንድትሆኑ እመኛለሁ፡፡ የዓለም መሪ ማለት የሰላም መሪ መሆን ማለት ነው፡፡”

ምንም እንኳ ዘለንስኪ የአየር ቀጠናው ነጻ እንዲሆን የተማጸኑ ቢሆንም ዩናይትድ ስቴትስ ግን ይህን በመደገፍ ሁኔታዎችን ለማመቻቸትም ሆነ ጀቶችን ለመላክ ፈቃደኛ አይደለችም፡፡

በውጭ ግንኙነት ጉዳዮች ምክር ቤት ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ስቴፈን ቢድል እንዲህ ይላሉ

“ዩክሬናውያኑ ትልቅ ስጋት የሆነባቸው የተለመደው መድፍ መደበኛው ሚሳዬልና መደበኛው እግረኛ ጦር ነው፡፡ የአየር ክልል ላይ እንዳይጣስ የበረራ እቀባ መጣሉ የዚያን ያህል ምንም ተጽዕኖ አይኖረውም፡፡ ስለዚህ በምድር ላይ ያለውን ወታደራዊ ግጭት እንዲባባስ ምክንያት በመሆን የበለጠ አደጋ ይፈጥራል፡፡የፖላንድን ተዋጊ ጀቶች ወደ ዩክሬናውያኑ ማስተላለፍም ተመሳሳይ ውጤት ነው የሚኖረው፡፡

ትናንት ረቡዕ የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር ሎይድ ኦስተንን ጨምሮ የኔቶ መከላከያ ኃላፊዎች ብራስልስ ውስጥ ተሰብሰበዋል፡፡

ሞስኮ ጥቃቷን የኔቶ አባል ወደሆኑት አገሮችም ልታስፋፋ ትችላለች የሚል ስጋት በመኖሩ አባል አገሮቹ ተሰብስበው የሩሲያን እርምጃ ማቆም የሚችሉበትን አዳዲስ እቅዶች መንደፍ እንደሚገባቸው የኔቶ ዋና ጸሀፊ ጀኔራል ስቶልትንበርግ

“ሁሉንም አጋሮቻችንን ለመከላከል ዝግጁ መሆናችንን በማስረዳት ሞስኮ ያላትን የተሳሳተ ስሌት እንድትረዳ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡” ሲሉ ተናግረዋል፡፡

በምክር ቤቱ ከጸደቀው የ13.6 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 4 ቢሊዮን ዶላሩ በጦርነቱ ሳቢያ ከዩክሬን ለተፈናቀሉት ወደ 3 ሚሊዮን ለሚጠጉ ሰዎች ሰብዓዊ እርዳታ የሚውል መሆኑ ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG