በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በዩክሬን ሩሲያ ጉዳይ የአውሮፓ አገሮች የተስማማ አቋም ይዘዋል ተባለ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን
የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን

ሩሲያ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ ምስራቅ አውሮፓ አገሮች 8ሺ500 መቶ ወታደሮችን ለማሰማራት ማቀዷን ሩሲያ በታላቅ ትኩረት እየተከታተለቸው መሆኑን አስታወቀች፡፡

የክሬምሊን ቃል አቀባይ ዲምትሪ ፔስኮቭ ዩናይትድ ስቴትስ የሩሲያ ዩክሬይንን ውጥረት እያባባሰች ነው የሚለውን የሩሲያ ክስ ደግሞ ማሳመታቸውም ተመልክቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ትናንት ሰኞ ቁልፍ ከሆኑ የአውሮፓ አገራት መሪዎች ጋር ሩሲያ በዩክሬን ድንበር ዙሪያ ስለምታደርገው የወረራ ስጋት ተነጋግረዋል፡፡

ዋይት ሀውስ ባወጣው መግለጫ የአውሮፓ አገራት በሩሲያ ዩክሬን ጉዳይ የጋራ ስምምነት ያላቸው መሆኑን አስታውቋል፡፡

ከእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ጽ/ቤት የወጣው መግለጫ መሪዎቹ እየጨመረ ባለው የሩሲያ ጠብ አጫሪነት ጉዳይ ላይ ዓለም አቀፍ አንድነት አስፈላጊ መሆኑን መስማማታቸውን አስታውቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስትር ሎይድ ኦስትን በምስራቅ አውሮፓ የተሰማሩት 8ሺ500 የዩናይትድስ ስቴትስ ወታደሮች በተጠንቀቅ እንዲቆዩ አዘዋል፡፡

XS
SM
MD
LG