በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንክን ዩክሬንን ጎበኙ ሩሲያም ውጥረቱን እንድታረግብ አሳሰቡ


የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪም እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን
የዩክሬን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪም እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን

ዩክሬንን የጎበኙት የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን ሩሲያ ግልጽ ምርጫ ቀርቦላታል ግጭቱን ለማርገብ የዲፕሎማሲውን መንገድ የማትከተል ከሆነ የከፋ አጸፋ ይከተላታል ሲሉ ተናገሩ፡፡

ብሊንክን ይህን የተናገሩት ዛሬ ኪየቭ ውስጥ ከዩክሬይን ፕሬዚዳንት ዘለንስኪ ጋር በተገናኙበት ወቅት መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ብሊንከን ዩናይትድ ስቴትስ የዩክሬን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲጠበቅ ያላትና ቁርጠኛ ድጋፍ ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል፡፡

ብሊንክን አያይዘውም የዩክሬንን የወደፊት እጣ ለመወሰን መብቱ ያላቸው ዩክሬኒያን ራሳቸው ብቻ ናቸው ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ዘለንስኪም የባይደን አስተዳደር ለዩክሬን የሚሰጠው ወታደራዊ ድጋፍ እንዲጨምር በማድረጉ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ባለሥልጣና ዛሬ ረቡዕ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ የባይደን አስተዳደር ባላፈው ወር ለዩክሬይን የ200ሚሊዮን ዶላር ተጨማሪ የወታደራዊ ደህንነት እርዳታ ማድረጉን አስታውቀዋል፡፡

ብሊንከን ፕሬዚዳንቱን ከማግኝታቸው በፊት በዩክሬይን ለሚገኙ የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሰራተኞች በጠንክራው የዲፕሎማሲ ጥረት ውጥረቱ ይረግባል የሚል ተስፋ ያላቸው ቢሆንም ምርጫው ግን የሩሲያ ነው ማለታቸው ተመልክቷል፡፡

ሩሲያ በዩክሬን ድንበር አቅራቢያ 100ሺ የሚጠጋ ጦሯን ማስፈሯ ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG