በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ህግ አውጭዎች ዋይት ሃውስ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ እንዲሰጥ ጠየቁ


የሪፐብሊካን የምክር ቤት አባል ማይክል ዎልትዝ
የሪፐብሊካን የምክር ቤት አባል ማይክል ዎልትዝ

ዩዩክሬንን ጎብኘተው የተመለሱ የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት በዲፕሎማሲ ጥምዘዘና በማዕቀብ ማስፈራሪያ ብቻ ለወረራ የተዘጋጁትን የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን እርምጃ ማቆም አይቻልም ሲሉ ተናገሩ፡፡

ባለፈው ቅዳሜና እሁድ ኪየቭን ጎብኝተው የተመለሱት የዴሞክራትና የሪፐብሊካን ህግ አውጭዎች ቡድን አባላት ከዩክሬን ልዩ ኃይል አዛዥና የዩክሬንን ብሄራዊ ጦር ከሚያሰለጥኑት የዩናይትድ ስቴትስ አባላት ጋር የተነጋገሩ መሆናቸው ተዘግቧል፡፡

ያለው ሁኔታ “እጅግ አሳሳቢ ነው” ያሉት የምክር ቤቱ አባላት፣ ዋይት ሃውስ የራሽያን ወረራ ለማስቆም የዩክሬንን ኃይል የሚያጠናክር የጦር መሳሪያ በአስቸኳይ መላክ ይኖርበታል ብለዋል፡፡

የሪፐብሊካን የምክር ቤት አባል ማይክል ዎልትዝ ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት “ጠንካራ እርምጃ እንደሚወሰድ ቃል መግባት፣ በተለይ ወረራው ከተፈጸመ በኋላ፣ በፑቲን ስሌት የሚያደርሰው ጉዳት እጅግ አነስተኛ ሆኖ የታያቸው ይመስለኛል፡፡”

የዴሞክራቱ ሴት ሞልተንም ዋይት ሃውስ ሩሲያ ዩክሬንን ብትወር ጠንካራ እርምጃ የተወሰደባት መሆኑን እንዳታውቅ የሚያደርግ እምርጃ መውሰድ እንዳለበት አሳስበዋል፡፡ “እኔ የምፈልገው ፑትን ዩክሬንን ከወረረ በሚቀጥሉት አምስት ደቂቃዎች የለስላሳ መጠን ከማሽናቸው ውስጥ ማውጣት የሚቸገሩ መሆኑን እንዲያውቁ ነው ፡፡ እንጂ ኔቶ ከወረራው በኋላ ጉባኤ ተቀምጦ ይህን ጉዳይ ምን ማድረግ ይኖርብናል? ብሎ እንዲከራከር አይደለም” ብለዋል፡፡

የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ "እኛ ይህን ጉዳይ መያዝ የምንፈገው ግጭቱን በሚያረግብ መልኩ በዲፕሎማሲያው መንገድ ነው" ብለዋል፡፡

የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታገን ትናንት በሰጠው መግለጫ ሩሲያ ግጭቱን ለማርገብ ከዩክሬን ድንበር አካባቢ ኃይሏን ወደ ኋላስ ታንቀሳቅስ የሚሳያ ምንም ምልክት አላየንም ብለዋል፡፡

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ኔቶ ወደ ምስራቅ አውሮፓ መስፋፋቱን የሚያቆምና በጎረቤት በተለይም እንደ ዩክሬን ባሉ አገሮችላይ የጦር መሳሪያውን የማይተክል መሆኑን በህግ ማረጋገጫ ከሰጠን የዲፕሎማሲ ግንኙነቱን በአስቸኳይ እንጀምራለን ማለታቸው ታውቋል፡፡

የሩሲያ ረዳት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ትናንት በሰጡት መግለጫም ኔቶ ወደ ምስራቅ የሚያደርገውን መስፋፋት የሚያቆም መሆኑን ዋስትና የማይሰጠን ከሆነ ሩሲያ ታክቲካል የኒዮክሌየር ጦር መሳሪያዎችን ጨምሮ ወታደሮችዋን የምታሰማራ መሆኑን ማስጠነቀቃቸው ይታወቃል።

XS
SM
MD
LG