በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በፓኪስታን ጎርፍ አደጋ ለተጎዱ የ10 ሚሊዮን ዶላር


የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከ

የዩናትድ ስቴትስ በጎርፍ አደጋ ለተጠቃቸው ፓኪስታን ተጨማሪ የገንዘብ እርዳታ እንደምታደርግ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን አስታወቁ፡፡

ብሊንከን በደረሰባት የጎርፍ አደጋ የተጎዳቸው ፓኪስታን አበዳሪዎች የብድር እፎይታና ዕዳ አከፋፈሏን መልሰው እንዲያዋቅሩላት እንደ ቻይና የመሳሰሉትን ትላልቅ አበዳሪዎችዋን እንድትጠይቅ ገፋፍተዋል፡፡

ብሊከን ትናንት ሰኞ ምሽት ዋሽንግተን ውስጥ ከፓኪስታን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቢላዋል ቡቶ ዛራዲን ጋር በበርካታ የጋርዮሽ ጉዳዮች ላይ መወያያታቸው ተመልክቷል፡፡

የጋራ ጉዳያቸው ስለሆነው በአፍጋኒስታን በፀረ ሽብርተኝነት ትብብርና ኢስላማባድ ከህንድ ጋር ስላላት ውጥረት የሞላበት ግንኙነቶችም ላይ መምከራቸውን ብሊንከን ተናግረዋል፡፡

ብሊንከን በዩናይትድ ስቴትስና በፓኪስታን መካከል ያለውን የ75 ዓመት ግንኙነት ምክንያት በማድረግ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ጽ/ቤት ውስጥ በሰጡት መግለጫ በፓኪስታን ለደረሰው የጎርፍ አደጋ “ከ56 ሚሊዮን ዶላር በላይ አፋጣኝ የሰብአዊ እርዳታ አሰባስበናል” ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አያይዘውም፣ ወደ 17 በሚደርሱ አውሮፕላኖች ምግብና ለመጠለያ የሚሆኑ ድንኳኖችና ቁሳቁሶችን አቅርበናል፡፡

ዛሬም ሌላ የ10 ሚሊዮን ዶላር የምግብ ደህንነት ዋስትና እርዳታ ይፋ ሳደርግ ደስታ ይሰማኛል” ማለታቸው ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG