በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በህግ አስከባሪዎች ስለ ግል ሃይማኖታቸው የተጠየቁ ሦስት አሜሪካውያን ሙስሊሞች ክስ መሰረቱ


ፎቶ ፋይል፦ መንገደኞች በሎስ አንጀለስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የፍተሻ ጣቢያውን ለማለፍ ተሰልፈው
ፎቶ ፋይል፦ መንገደኞች በሎስ አንጀለስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ የፍተሻ ጣቢያውን ለማለፍ ተሰልፈው

ሦስት አሜሪካውያን ሙስሊሞች ከነበረን የዓለም አቀፍ ጉዞ ስንመለስ የዩናይትድ ስቴትስ የድንበር ጥበቃ ህግ አስከባሪዎች ሃይማኖታችንን እንድንነግራቸው በመጠየቅ ህገመንግሥታዊ መብታችንን ተጋፍተዋል በሚል ክስ መመስረታቸው ተነገረ፡፡

ከሜኒሶታ፣ ቴክሳስና አሪዞና የሆኑት ሦስቱ አሜሪካውያን በአገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስቴር ሠራተኞ ላይ ክሳቸውን የመሰረቱት ሎስ አንጀለስ በሚገኘ የፌዴራሉ ፍርድ ቤት መሆኑም ተመልክቷል፡፡

የተመሰረተው ክስ የሰዎችና የእምነት ነጻነትና የእኩል መብት ባለቤትነት ጥበቃን የሚጥስ መሆኑን እንደሚገልጽ ተነገሯል፡፡

በተለይ ከቴክሳስ የሆኑት ከሳሽ እኤአ በ2019 በሎስ አንጀለስ አውሮፕላን ማረፊያ ከውጭ ጉዟቸው ሲመለሱ እምነታቸውን እንዲገልጹ የተጠየቁ ሲሆን፣ እርሳቸው፣ ስልካቸውና ማስታወሻቸው ሳይቀር መበርበራቸውን ገልጸዋል፡፡

ከሚኒሶታ የብሉሚንግተን በሚገኝ መስጊድ ኢማም የሆኑት የመጡት ከሳሽ አብርዱረህማን ኤደን ካሪዬም እንዲሁ ወደ አገር በተመለሱባቸው እኤአ ከ2017 እስከ 2022 ባሉት ጊዜያት ቢያንስ አምስት ጊዜ መጠየቃቸውን ተናግረዋል፡፡

ከሳሾቹን የወከለው የዩናይትድ ስቴትስ የሲቪል ነጻነት ህብረት ጥያቄዎቹ የሰዎቹን ህገመንግሥታዊ መብት የሃይማኖት ነጻነትና የእኩል ጥበቃ መብታቸውን የጣሱ ናቸው ብሏል፡፡

XS
SM
MD
LG