በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ብሊንከን ከጀርመኑ አቻቸው ጋር በአፍጋኒስታን ጉዳይ እየተወያዩ ነው


የዩናይድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን
የዩናይድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን

የዩናይድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን እና የጀርመኑ አቻቸው የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር ሄይኮ ማስ ከሌሎች አጋር ቡድኖች ጋር በመሆን ዛሬ ዕሮብ አፍጋኒስታን በታሊባን ከተያዘች በኋላ ለሃገሪቱ የሰብዓዊ ድጋፍ ስለሚደረግበት ሁኔታ እየተወያዩ ነው፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ቢሮ ከስብሰባው መጀመር በፊት ባወጣው መግለጫ የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ምላሽ እና የታሊባን ቃልኪዳኑን የመጠበቁ ጉዳይ የስብሰባው አንድ የመወያያ ርዕስ እንደሚሆን አስታውቋል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ የውጪ ጉዳይ ሚኒስተር አንተኒ ብሊንከን ከኳታር ወደ ጀርመን ከማቅናታቸው በፊት ታሊባን ሕጋዊ የጉዞ ሰነድ ያላቸውን እና ከሃገር መውጣት ለሚሹ አፍጋኒስታናዊያንን ለማስወጣት የገባውን ቃል እንዲያከብር አሳስበዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የውጪ ጉዳይ ቢሮው በዛሬው ስብሰባ በአፍጋኒስታን ስላለው የሰብዓዊ መብቶች እና የጸረ ሽብር ጦርነትን በተመለከተ እንደሚወያዩም አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG