በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፍሎሪዳ ውስጥ የመኖሪያ ህንጻ መደርመስ አደጋ የሟቾች ቁጥር 12 ደረሰ


ፍሎሪዳ ማያሚ አቅራቢያ ሰርፍሳይድ ውስጥ የፈረሰው ቻምፕሌይን ታወርስ
ፍሎሪዳ ማያሚ አቅራቢያ ሰርፍሳይድ ውስጥ የፈረሰው ቻምፕሌይን ታወርስ

ዩናይትድ ስቴትስ ፍሎሪዳ ክፍለ ሃገር ውስጥ በተደረመሰው የመኖሪያ ህንጻ የሞቱት ሰዎች ቁጥር አስራ ሁለት ደረሰ።

ፍሎሪዳ ማያሚ አቅራቢያ ሰርፍሳይድ ውስጥ በፈረሰው ኮንዶሚኒየም አደጋ አንድ መቶ አርባ ዘጠኝ ሰዎች አሁን የደረሱበት አለመታወቁ ተገልጿል።

የአደጋውን ሰለባዎች ፈልገው ለማትረፍ የተሰማሩት ሰራተኞች አሁንም ጥረታቸውን እንደቀጠሉ የማያሚ ዴድ ከንቲባ ትናንት ማታ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል።

ቻምፕሌይን ታወርስ የተባለው አንድ መቶ ሰላሳ ስድስት ቤቶች ያሉት ባለ አስራ ሁለት ፎቅ ኮንዶሚኒየም ህንጻ ባለፈው ሳምንት ነው በአንድ ጎኑ በኩል የፈረሰው።

ከንቲባው እንዳስረዱት የፈጥኖ ለእርዳታ ደራሽ ሰራተኞቹ በክሬኖች በተለዩ ማብሪያዎች እና በሰለጠኑ ውሾች እየተጠቀሙ ፍለጋቸውን ቀጥለዋል።

ፕሬዚደንት ጆ ባይደን እና ቀዳማዊት እመቤት ጂል ባይደን ነገ ሃሙስ አደጋው ወደደረሰባት ሰርፍሳይድ ከተማ እንደሚጓዙ የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ጄን ሳኪ አስታውቀዋል።

የአደጋውን ሰለባዎች ፈልጎ ለማዳን የተሰማሩትን ያማሰግናሉ ከሰለባዎቹ ቤተሰቦች ጋርም ተገናኝተው ይወያያሉ ብለዋል።

XS
SM
MD
LG