በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን በአውሎ ንፋስ ጉዳት የደረሰባትን ኬንታኪን ይጎበኛሉ


በተከሰተው ከባድ የአውሎ ነፋስና ዝናብ የፈራረሰው አካባቢ ኬንታኪን
በተከሰተው ከባድ የአውሎ ነፋስና ዝናብ የፈራረሰው አካባቢ ኬንታኪን

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ባለፈው ዓርብ በተከሰተው ከባድ የአውሎ ነፋስና ዝናብ ከተጠቁ አካባቢዎች ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባት፣ 64 ሰዎች የሞቱባትና በብዙ ሺዎች የተፈናቀሉባትን ኬንታኪን ለመጎብኘት ወደዚያው እንደሚያመሩ ተገለጸ፡፡

ለኬንታኪ የአስቸኳይ ጊዜ እርዳታ ያወጁ መሆኑን የገለጹት ባይደን ጉዳት ለደረሰባት የኢሌኖይ ክፍለ ግዛት ተመሳሳዩን እንደሚደርግ ተናግረዋል፡፡

ለኬንታኪም ሆነ ሌሎቹን ክፍለ ግዛቶች ለመታደግ የአስተዳደራቸው ሰዎች የሚያስፈልገውን ሁሉ እንዲያደርጉ ማዘዛቸውንም ባይደን ገልጸዋል፡፡

የፌዴራል አስቸኳይ ጊዜ አስተዳደር ተቋም/FEMA/ በኬንታኪው አውሎ ነፋስ ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸውን ቤቶች ለመጠገን በእያንዳንዱ ቤት እስከ 35 ሺ ዶላር ወጭ የሚያደርግ መሆኑን አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG