በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባይደን ስለ ስደተኞች አፍጋኒስታን ቻይናና ሰሜን ኮሪያ ተናገሩ


ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ዋይት ሐውስ ውስጥ ትናንት ሀሙስ እኤአ መጋቢት 25/2021 ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ጥያቄና መልስ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን፣ ዋይት ሐውስ ውስጥ ትናንት ሀሙስ እኤአ መጋቢት 25/2021 ለመጀመሪያ ጊዜ ከጋዜጠኞች ጋር ባደረጉት ጥያቄና መልስ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ሥልጣን ከያዙ በኋ ላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫቸው፣ በዩናይትድ ስቴትስና ሜክሲኮ ድንበር በኩል፣ ቁጥራቸው እየጨመረ የመጣውን ስደተኞችና ፣ አሜሪካ ወታደሮችዋን ከአፍጋኒስታን ለማውጣት ያስቀመጠቸውን፣ እኤአ ግንቦት 1 ቀነ ገደብ የማትጠብቅ መሆኑን ማስታወቋን አስመልከቶ፣ ከጋዜጠኞች ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች ቀርበውላቸዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ወደ ሥልጣን ከመጡ በኋላ የመጀመሪያቸው በሆነው ጋዜጣዊ መግለጫቸው አብይ መነጋገሪያ የነበረው የስደተኞች ጉዳይ ነበር፡፡

ፕሬዚዳንት ባይደን በጉዳዩ ላይ ያላቸው አቋም የተለሳለሰ ነው የሚለውን ምልከታ አልተቀበሉትም፡፡

በሜክሲኮ በኩል ወደ አሜሪካ የሚገቡ ስደተኞች ቁጥር ግን እየጨመረ መጥቷል፡፡ ስለዚሁ ሁኔታ ሲናገሩ ባይደን እንዲህ ብለዋል

“የሚመጡት እኮ ለዚህ ነው ምክንያቱም ባይደን መልካም ሰው እንደሆነ ያውቃሉዋ!! ያለው እውነት ግን የተለወጠ ነገር የለም፡፡ ብዙ ሰዎች የመምጣታቸውን ያህል በኔ አስተዳደር በድንበር በኩል የመጡት ስደተኞች ቁጥር በ28 ከመቶ ሲጨምር፣ ከኮቪድ ወረርሽኝ በፊት በነበረው የ2019 ዓም የትራምፕ አስተዳደር ጊዜ 31 ከመቶ ነበር የጨመረው፡፡”

በዚህ ሳምንት መጨረሻ ላይ ባይደን የስደተኞቹ ቁጥር የጨመረበትን ትክክለኛ ምክንያት እንዲከታተሉ ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስን ሰይመዋል፡፡

የውጭ ግንኙነቱን አስመልከቶ ዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮችዋን ከአፍጋኒስታን ለማውጣት ያስቀመጠችውን የ እኤአ ግ ንቦት 1 ቀነ ገደብ ማክበር እንደማትችል አስታውቀዋል፡፡ በምትኩም ያስቀመጡት ወይም የጠቀሱት ቀን የለም፡፡ ብዙ አለመቆየታቸውን በመግለጽ ይህን ብለዋል

“እንዴትና በምን ሁኔታ ውስጥ ሆነን ነው ፣ ቀድሞውኑም እንደዚያ ያለ የአወጣጥ ስምምነት ውስጥ እንዴት ተገባ በሚያሰኝ ሁኔታ በፕሬዚዳንት ትራምፕ የተደረገውን ስምምነት ማስፈጸም የምንችለው? ለማንኛውም ግን ብዙ አንቆይም፡፡

አፍጋኒስታን ውስጥ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እየጨመረ ከመጣው ግጭት አንጻር መግለጫው አንዳንዶቹን ታዛቢዎች አላስደነቀም፡፡ ከ እነዚህ መካከል የዓለም አቀፍ ጉዳዮችና የስትራቴጂ ተቋም ውስጥ፣ የዓለማ አቀፋዊ ግጭቶች ባለሙያው የሆኑት አንተኒ ካርድስማን አንዱ ናቸው ፡፡ እንዲህ ይላሉ
“ያለው ተጨባጭ ሁኔታ የፕሬዚዳንት ባይደን አስተዳደር ሥልጣኑን በተረከበበት ወቅት ጭራሽ የተባባሰውን ግጭት አስወግዶ ውጊያውን በማቆምም ሆነ የሰላም ሂደቱን ገጽታ የሚያመላከት አንዳች ነገር ለማስመዝገብ ያደረግነው ምንም ነገር የለም፡፡”

የዩናይትድ ስቴትሱ መሪ ባይደን፣ ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ በምስራቃዊ የአገሪቷ ግዛት በኩል፣ ሁለት የቅርብ ርቀት ተወንጫፊ የባለስቲክ ሚሳኤሎችን ማስወንጨፏን የተባበሩት መንግሥታት ውሳኔዎች የጣሰ ነው ብለውታል፡፡ አስከትለውም፦

“ይህን ነገር ማባባሱን ከመረጡ ምላሽ ሊኖር ይችላል፡፡ አጸፋውን እንዳመጣጡ እንመልሳለን፡፡ ይሁን እንጂ ግን የተወሰነ መልክ ላለው ዲፕሎማሲም ተዘጋጅቻለሁ፡፡”

ባይደን ስለ ስደተኞች፣ አፍጋኒስታን፣ ቻይናና ሰሜን ኮሪያ ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:33 0:00


ፕሬዚዳንት ባይደን እንዲሁም የቻይናው አቻቸው ዚ ጄፒንግ ዓለም አቀፍ ህግ ጋትን እንዲያከበሩ ከአጋሮቻቸው ጋር ሆነው ግፊት እንደሚያደርጉ ተናግረው ይህን ብለዋል፡፡

“በተለያዩ በርካታ አጋጣሚዎች ግጭት የማንፈልግ መሆኑን ለራሳቸው በግል ነግሬያቸዋለሁ፡፡ ምን እንኳ ጠመዝማዛና አስቸጋሪ ውድድር መኖሩን ብናውቅም ማለት ነው፡፡”

የዓለም አቀፋዊ ግጭቶች ባለሙያው የሆኑት አንተኒ ካርድስማን ቻይናን አስመልክቶ የተለወጠ ነገር መኖሩን ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል

“ቻይናን አስመልከቶ ያለው ንግግር ትኩረቱን እየቀየረ የመጣ ይመስለኛል፣ ከንግድና በወታደራዊ ግጭቶች ፍጥጫ በመራቅ ከቻይና ጋር መወዳደር ወደሚያስችል ግንኙነቶች ላይ ያተኮረ ይመስለኛል፡፡”

በጋዜጣው መግለጫው ላይ ለአንድ ሰዓት ያህል የቆዩት ፣ ፕሬዛዳንት ባይደን በመጀመሪያዎቹ የሥልጣን ዘመናቸው 100 ቀናት ውስጥ 200 ሚሊዮን የሚደርሱ የኮቪድ 19 ክትባቶችን በየሰው ክንድ ላይ እንደሚያሳርፉ ተናግረዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2024 ምክትል ፕሬዚዳንት ከማላ ኻሪስን አስከትለው በድጋሚ እንደሚወዳደሩም ይጠበቃል፡፡

መግለጫውን የተከታተለችው የቪኦኤ የዋይት ሐውስ ዘጋቢ ፓትሲ ውዳክስዋራ ከዘገበችው የተወሰደ፡፡

XS
SM
MD
LG