በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከአትላንታው ጥቃት ጋር በተያያዘ ተጠርጣሪ ግለሰብ ተያዙ


ዩናይትድ ስቴትስ ጆርጂያ ክፍለ ግዛት አትላንታ ከተማ ስምንት ሰዎች ከተገደሉበት ጥቃት በተያያዘ ፖሊሶች አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውን አስታወቁ።

ከተገዱት መካከል ስድስቱ የትውልድ መሰረታቸው እስያ የሆኑ ሴቶች ሲሆኑ የደቡብ ኮሪያ የውጭ ጉዳይይ ሚኒስቴር አራቱ ሰለባዎች ትውልደ ኮሪያ መሆኑን አመልክቷል።

የዋይት ሃውስ ቃል አቀባይ ዛሬ ማለዳ በሰጡት ቃል ፕሬዚዳንትጆ ባይደን ስለጥቃቶቹ ትናንት ሌሊት ገለጻ የተደረገላቸው መሆኑ አመልክተዋል፥ የዋይት ሃውስ ባለሥልጣናት ከአትላንታ ከንቲባ ጋር መነጋገራቸውን እና ከፌዴራል ምርመራ ቢሮ ጋር መነጋገራቸውን እንደቀጠሉ ጄን ሳኪ ጨምረው አስታውቀዋል።

የመጀመሪያው ጥቃት የተፈጸመው ከአትላንታ ከተማ በስተሰሜን ወደሃምሳ ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ በሚገኝ የመታሻ ቤት/ማሳጅ ቤት/ ሲሆን አጥቂው ተኩስ ከፍቶ ሁለት መሰረታቸው እስያ የሆኑ ሴቶች ፤ እንዲት ነጭ ሴት እና አንድ ነጭ ወንድ ገድሏል፤ አንድ ሌላ ወንድ በጥቃቱ ቆስሏል።

ከአንድ ሰዓት ገደማ በኋላም የአትላንታ ፖሊሶች በአንድ መዋቢያ ቤት በጥይት የተገደሉ የሦስት ትውልደ እስያ ሴቶች አስከሬኖች አግኝተዋል። ከዚሁ ስፍራ በጥቂት ርቀት በሚገኝ የመታሻ ማዕከል ደግሞ አንዲት እስያዊት ተገድለው ተገኝተዋል።

የተጠርጣሪው መኪና በሦስቱም ስፍራዎች እንደነበረ በስፍራዎቹ ባሉት የጥበቃ ካሜራዎች በተቀረጹ ምስሎች ላይ መታየቱን የገለጹት ፖሊሶች ሁሉም ቦታዎች ላይ ተኩስ የከፈተው ያው አጥቂ መሆኑን እርገጠኞች ነን ብለዋል።

ፖሊሶች አውራ ጎዳና ላይ ተከታትለው በማሳደድ ከአትላንታ በስተደቡብ 240 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኝ ስፍራ ተሽከርካሪውን አስቆመው ሮበርት ኤረን ሎንግ የተባለ የሃያ አንድ ዓመት ሰው ይዘዋል።

ጥቃቱን ለመፈጸም አጥቂውን ያነሣሳው ምን እንደሆን ለጊዜው አልታወቀም። ይህ የአትላንታው ጥቃት የደረሰው ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ መሰረታቸው ከወደእስያ በሆኑ ሰዎች ላይ የሚደርሰው ጥቃት እየተበራከተ ባለበት በዚህ ወቅት መሆኑ ነው።

XS
SM
MD
LG