በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፔንታገን በአፍጋኒስታን በደረሰው የድሮን ጥቃት ስህተት አባላቱ እንደማይቀጡ አሳታወቀ


ፎቶ ፋይል፦ ሎይድ ኦስተን
ፎቶ ፋይል፦ ሎይድ ኦስተን

ባለፈው ነሃሴ ወር በአፍጋኒስታን በዩናይትድ ስቴትስ ድሮን ለተገደሉ 10 ሰላማዊ ሰዎች የዩናይትድ ስቴትስ መከላከያ ሚኒስቴር፣ ፔንታገን አደጋውን ያደረሱትን የሠራዊቱን አባላት እንደማይቀጣ አስታወቀ፡፡

ከዚህ ውሳኔ የተደረሰው የመከላከያ ሚኒስትሩ ሎይድ ኦስተን ከሁለት የበላይ አዛዦች የቀረበላቸውን አስተያየት ካጸደቁ በኋላ መሆኑ ተነግሯል፡፡

የፔንታገን ቃል አቀባይ ጆርን ከርቢ ለቪኦኤ ለቀረበላቸው ጥያቄ እንደተናገሩት የመከላከያ ሚኒስትሩ በጉዳይ ላይ ተጨማሪ የተጠያቂነት ምርመራ እንደማይፈቅዱ ማስታወቃቸውን ገልጸዋል፡፡

ፔንታገን ገለልተኛ መርማሪ መድቦ ሁኔታውን ካጣራ በኋላ እኤአ ነሀሴ 29 የተፈጸመው አደጋ “አስዛኝ ስህተት ነው” ብሏል፡፡

“የተፈጸመው ስህተት የተሳሳተ መረጃን አምኖ ከመቀበል እንጂ ከንዝህላልነት ወንጀል የተከሰተ ነው ብሎ እንደማያምንም” ፔንታገን አስታውቋል፡፡

በወቅቱ አንድ አጥፍቶ ጠፊ ከሀሚድ አውሮፕላን ማረፊያ አቅራቢያ 13 አሜሪካውያንን ጨምሮ 170 የአፍጋን ሰዎችን በገደለበት ማግስት በተካሄደ የድሮን ጥቃት ሰባት ህጻናትን ጨምሮ 10 ሰዎች መሞታቸው ይታወቃል፡፡

XS
SM
MD
LG