በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ለአፍጋኒስታን መልሶ ግንባታ ትሪሊዮን ዶላሮች ቀልጠዋል”


“ለአፍጋኒስታን መልሶ ግንባታ ትሪሊዮን ዶላሮች ቀልጠዋል”
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:02 0:00

“ለአፍጋኒስታን መልሶ ግንባታ ትሪሊዮን ዶላሮች ቀልጠዋል”

አንድ ከፍተኛ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት መርማሪ ሁለቱንም የዴሞክራቲክ እና የሪፐብሊካን ፓርቲ አስተዳደሮችን ጥረትና ትኩረት ያገኘው የአፍንጋኒስታን ጉዳይ ትልቅ ውድቀትና በትሪሊዮኖች የሚቆጠር ዶላር የጠፉበት መሆኑን ለህግ አውጭዎቹ የምክር ቤት አባላት ተናግረዋል፡፡

የመርማሪው ባለሙያው ምስክርነት የመጣው የምርክቤት አባላቱ ዩናይትድ ስቴትስ በዚህ ዓመት ከአፍጋኒስታን ለቃ የወጣችበት መንገድ ለምን በቀውስ የተሞላ እንደነበር መመርመር በያዙበት ወቅት ነው፡፡

አፍጋኒስታንን በማስተዳደር ሁለተኛ ወራቸውን ያስቆጠሩት ታሊባኖች ድርቅ፣ የኢኮኖሚ አለመረጋጋትና ያልተቋረጠው ሁከትና ጥቃት ከፊታቸው ተደቅኗል፡፡

ይህ ዩናይትድ ስቴትስ በአፍጋኒስታን በ20 ዓመታት ውስጥ ያደረገችው ነገር ከምኔው በፍጥነት ተሸርሽሮ እንደጠፋ ያሳያል፡፡ ለእገዛው በትሪሊዮኖች የሚቆጠር ዶላሮች የወጣበትን ውጤት ለመርመር የተቀመጡት ህግ አውጭዎቹ የምክር ቤት አባላትም በዚህ ሳምንት ከከፍተኛው የመርማሪ አካል የተመለከቱት ገጽታ እጅግ የደበዘዘ ነው፡፡

ጆን ሶፕኮ የአፍጋኒስታን መልሶ መንገባት ልዩ ተቆጣጣሪ ጀኔራል ናቸው፡፡ እንዲህ ይላሉ

“ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት የአፍጋንን የፖለቲካ ባህል አልተገነዘቡም፡፡ በዚህ የተነሳ በሙስና የተበተቡ ፖለቲከኞችና ሥልጣን አፈላላጊዎችን እንዲጎለብቱ አደረጓቸው፡፡”

ሶፕኮ፣ እየተተካኩ የቀጠሉት ሁለቱም የዩናይትድስ ስቴትስ የዴሞክራቲክ እና የሪፐብሊካን አስተዳደሮች ሁል ጊዜም አፍጋኒስታንን መልሶ የመገንባቱ ስኬት እየተቃረበ ነው ቢሉም፣ ለሁለት አስርት ዓመታት የተደረገው ጥረት ያን ሁሉ ሀብቶ በልቶ ቀርቷል፡፡

ተቆጣጣሪው ጆን ሶፕኮ ይህንን ሲገልጹ

“ የማይታዩ መናፍስት ወታደሮች፣ የማይታዩ መናፍስት ፖሊሶች! እዚያ በቦታው በአካል በሌሉ ሰዎች ስም የአፍጋኒስታን መንግሥት ሲመሰረት አይተናል፡፡” ብለዋል፡፡

የሶፖኮ ምስክርነት የመጣው ፣የዩናትድ ስቴትስ ህግ አውጭዎች የባይደን አስተዳደር ከአፍጋኒስትን ለቆ የወጣበትን መንገድ በሚመረምሩበት ወቅት ነው፡፡

የሪፐብሊን ምክር ቤት አባል ማይክል መኩል እንዲህ ይላሉ

“ፕሬዘዳንት ባይደንና ባልሥልጣኖቻቸው ይገፉ የነበሩት በአፍጋኒስታን ያለው አማራጭ ሁለት ብቻ እንደሆነ አድርገው ነበር፡፡ አንደኛ በዚህ በደምና በቀውስ በተሞላው መንገድ ሙሉ ለሙሉ ለቆ መውጣት ወይም በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ወታደሮችን ላልተውሰነ ጊዜ ዝምብሎ በቦታው መተው፡፡ እኔ ግን ከመነሻውም ይህ ጨርሶ ትክክለኛ አማራጭ አልነበረብ ብዬ አምናለሁ፡፡ በመጀመሪያ ፕሬዚዳንቱ የጸረ ሽብሩን ሥራ ብቻ የሚቆጣጠር ትንሽ ኃይል እንዲያስቀሩ በከፍተኛ ጀኔራሎቻቸው የተነገራቸውን ምክር መስማት ነበረባቸው፡፡”

ይሁን እንጂ ዴሞራቶቹ ፕሬዚዳንት ባይደን ጨርሶ የማይቻለውን ችግር ከሳቸው በፊት ከነበሩት አስተዳደሮች የወረሱት መሆኑን በመግለጽ ይከራከራሉ፡፡

የተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ሊቀመንበር ግሬግ ሚክስ አንዱ ናቸው፡፡ እንዲህ ይላሉ

“ፕሬዚዳንት ትራምፕና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትራቸው ፓምፔዮ ከታሊባን ጋር ያደረጉት ስምምነት በዚህ የበጋ ወቅት ለተፈጸመው የተዝረከረከ አወጣጥ በቀጥታ አስተዋጾ አድርጓል፡፡”

አንድ ተንታኝ በሺዎች የሚቆጠሩ የአፍጋን ረዳቶችን ወደ ኋላ የቀሩበትንና 13 የዩናይትድ ስቴትስ ወታደሮች የሞቱበትን የአወጣጡ ቀውስ ከመከሰቱ በፊት የባይደን አስተዳደር ሊያደርግ የሚችለው አማራጭ ነበረው ይላሉ፡፡

ይህን የሚሉት ከብሩኪንግ ተቋም ማይክ ኦ ሃንሎን ናቸው

“በዚያ ላይ ደግሞ ታሊባን ከአሽራፍ ጋኻኒ መንግሥት ጋር ሥልጣን ለመጋራት ጨርሶ ሊደራደር አልፈለገም፡፡ ይህ እኤአ መጋቢት 29 2020 ከፕሬዚዳንት ትራምፕ አስተዳደር ጋር የተደረሰበት ስምምነት የተጣሰበት ሌላኛው ማሳያ ነው፡፡ ስለዚህ እንደሚመስለኝ ፕሬዚዳንት ባይደንም ለታሊባኖች “ ፣ “ስሙ ለስምምነቱ እየተገዛችሁ አይደለም፡፡ ስለዚህ እኔም አላከብረውም” ማለት የሚችሉበት እድሉ ነበራቸው፡፡ አሁን ማድረግ የምንችለው ወደ የሰላሙ ንግግር ተግባራዊ ሊሆን ወደሚችልበት እንምጣ፣ ለምሳሌ ሥልጣን መጋራት የሚቻልበት መንገድ ካለ እናድርገው፡፡ ስለዚህ ያን በመቀበል ተግባራዊ ሊሆን የሚችልበት መንገድ ካለ ዩናዩትድ ስቴትስ ለቃ መውጣት የምትችልበትን መንገድ ማመቻቸት እንችላለን፡፡”

ሰባት የረፐብሊካን ሴነተሮች በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ልዩ መርማሪ ተቋቁሞ የባይደን አስተዳደር ከአፍጋኒስታን የወጣበትን መንገድ እንዲመረምር የሚያዘውን ረቂቅ ህግ ማስተዋወቃቸው ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG