በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"የትግራይ ግጭት እንዲያበቃ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ማሳደሩን ትቀጥላለች"


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊነክን
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊነክን

ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ወደ ስድስት ወር ገደማ የሆነውን ግጭት እንድታቆም ግፊት እያደረገች ነው፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት፣ ተባባሪ የሆኑ የኤርትራ ወታደሮች ከልሉን ለቀው እንዲወጡም ጥሪ አቅርባለች፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣን እንደተናገሩት፣ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ መንግሥት እየተባባሰ የመጣውን ሰአብአዊነትና እና የሰብአዊ መብት ቀውስ እንዲያቆሙ ጫና ለማሳደር ሲባል ከሰብአዊ እርዳታዎች ውጭ ለኢትዮጵያው የምታደርገውን ድጋፍ ማቋረጧን የምትቀጥል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳታ ሚኒስትር ሮበርት ጎዴክ ለቪኦኤ በስልክ እንደተናገሩት “ጦርነቱ መቆም አለበት፡፡ ችግር ሆኖ የቆየው የሰአብዊ እርዳታ የሚሰጥበት መንገድም መከፈት ይኖርበታል፡፡” ብለዋል፡፡

የትግራይ ግጭት እንዲያበቃ አሜሪካ ኢትዮጵያ ላይ ጫና ማሳደሩን ትቀጥላለች
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:46 0:00


የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ሚኒስትር ሮበርት ጎዴክ፣ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃል ጨምረው እንደተናገሩት፣

“የሰብአዊ መብት ጥቃቱና የሚደርሰው ግፉ እንዲቆም እንፈልጋለን፡፡ የኤርትራ እና የአማራ ሚሊሻ ለቀው እንዲወጡ እንፈልጋለን፡፡ ይህ ግጭት በእርግጥ እንዲቆም እንፈልጋለን፡፡” ብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ምኒስትሩ አንተኒ ብሊንከን ከኬኒያ እና ከናይጄሪያ ባለሥልጣኖች ጋር በድረ ገጽ ተወያይተዋል፡፡

በንግግሩ ከፍተኛው አጀንዳ የነበረው “ዴሞክራሲያዊ አስተዳደርን በማጠናከር” እና “ዘላቂ ደህንነትን በመገንባት” ዙሪያ መሆኑን፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስ ባወጡት መግለጫ አስታውቀዋል፡፡

በትግራይ ያለው ቀውስ “የቀጠናው ችግር ነው፣ በአጠቃላይ ቀጠናውም ላይ አደጋን ይደቅናል፡፡” በማለት የተናገሩት ጎዴክ፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ከሌሎች የአፍሪካ መሪዎች ጋር ይህን አስከፊ ችግር ለማቆም “በቅርበት እየተገናኘች” ነው ብለዋል፡፡

አብይ ዘመቻውን የጀመሩት፣ በትግራይ ክልል ላይ ባለፈው ህዳር ወር ውስጥ “ህግና ሥርዐት ማስከበር ዘመቻ” የሚል ስያሜ በመስጠት፣ በኢትዮጵያ የፌደራል ወታደሮች ካምፕ ላይ የተፈጸመውን ጥቃት አነሳስተዋል በሚል፣ የህወሃት አመራሮችን ለመያዝና ትጥቅ ለማስፈታት ነበር፡፡

ህወሃት የፖለቲካ ቡድን ሲሆን የፌደራል መንግሥቱን በቀጣይነት ለመዋጋት የወሰነ የታጣቂ ክንፎች ያሉት ድርጅት ነው፡፡ ህወሃት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ስር ሥልጣንን ተቆጣጥሮ የቆየ ድርጅት ነው፡፡

እኤአ መጋቢት 26፣ አብይ ኤርትራ ኃይሎችዋን ከትግራይ ለማስወጣት ተስማማታለች ብለው ነበር፡፡ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት ግን እንደሚሉት ለቆ መውጣቱ ተፈጻሚ ስለመሆኑ ምንም ማስረጃ የለም፡፡

ባለፈው ሰኞ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይን በስልክ ያነጋገሩት ብሊንከን “ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ለቀው እንዲወጡ የገቡትን ቃል በአስቸኳይ በግልጽ ሊረጋገጥ በሚችል መልኩ፣ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ እንዲደረግ ግፊት ማድረጋቸውን” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

አዲስ የተሰየሙት በዩናይትድ ስቴትስ የምስራቅ አፍሪካ ልዩ ልኡክ ጄፈሪ ፌልትማን፣ በሚቀጥሉ ቀናት ውስጥ ወደ ኢትዮጵያ ይጓዛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ባሳለፍነው ሰኞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለቪኦኤ እንደተናገሩት፣ ዩናይትድ ስቴትስ ከሰ አብአዊ እርዳትዎች ውጭ ለኢትዮጵያው የምስት ሰጣቸውን ድጋፎች ማቋረጧን የምትቀጥል ሲሆን፣ ለአገሪቱ የሚሰጡ የሰብአዊ እርዳታዎች ግን ትቀጥላለች ብለዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ስለዚሁ ሲናገሩ “አሁን በኢትዮጵያ ያለውን ሁኔታ ግምት ውስጥ በማስገባት፣ በሌሎች ፕሮግራሞች፣ ብዙዎቹ በደህንነት ጉዳዮች የምናደርጋቸው ናቸው፣ እነሱን ላለማቋረጥ ወስነናል፡፡” ብለዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ ባለፈው ዓመት፣ ኢትዮጵያ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ከግብጽ ጋር ያላትን አለመሰማማት ማስወገድ ባለመቻሏ፣ ለኢትዮጵያ የምት ሰጣቸውን የተወሰኑ የውጭ እርዳታዎች አቋርጣለች፡፡

ይሁን እንጂ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ “ዋሽንግተን በሰብአዊው ዘርፍ የምትሰጠውን እርዳታ ትቀጥላለች” ብሏል፡፡ አይይዞም “ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ላለው ዘላቂ አጋርነትና የኢትዮጵያን የግዛትና ብሄራዊ አንድነት” እንዲጠበቅ ቁርጠኛ መሆኑን ገልጿል፡፡

በትግራይ ክልል ያለው ግጭት፣ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት እና በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ፣ የአገር ውስጥ ተፈናቃይ እንዲሆኑ አድርጓል፡፡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ወደ አጎራባች ሱዳን እንዲሰደዱ አድርጓል፡፡ በተባበሩት መንግሥትታት በተገኘው መረጃ መሰረት የትግራይ ክልል ከ5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች የምግብ የውሃና የመድሃኒት እጥረት አለባቸው፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ትልቁ የሰአብአዊ እርዳታ ለጋሽ አገር ናት፡፡ በትግራይ ብቻ እጅግ ለተጎዱትና የሰብአዊ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች፣ ዩናይትድ ስቴትስ ወደ 305 ሚሊዮን ዶላር ለግሳለች፡፡

ትናንት ማክሰኞ፣ ብሊንከን የዩናይትድ ስቴትስ ከፍተኛ ዲፕሎማት ሆነው ለመጀመሪያው ጊዜ አፍሪካን በድረ ገጽ በተደገፈ የሚያደርጉትን ጉብኝት ጀምረዋል፡፡

ከወጣት አፍሪካ ተነሳሽነት መሪዎች ወይም ያሊ (YALI) አባላት ጋር ተገናኝተው እንደ ኢኮኖሚክ ልማት፣ ዴሞክራሲ መልካም አስተዳደር፣ የአየር ንብረት ለውጥ ጤናና በመሳሰሉት የተለያዩ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ዋናው ዲፕሎማት ከናይጄሪያው ፕሬዚዳንትና ሞሀመድ ቡዋሪ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጂኦፈሪ ኦኒያማ ጋር ተገናኝተው፣ ዴሞክራሲንና መልካም አስተዳደርን ለማጠናከር፣ ዘላቂ ደህንነትን በማስፈን፣ የኢኮኖሚ ትብብርን ለማጉላትና በተለያዩ መስኮች ለመስራት ባላቸው የጋራ ግቦች ላይ ይወያያሉ፡፡

ብሊንክን ከኬኒያ ባለሥልጣናት ጋር የሚገናኙ ሲሆን፣ 57 ዓመት ያስቆጠረውን የሁለቱ አገሮች ግንኙነት ያከብራሉ፡፡ ከፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬን ያታም፣ እንዲሁም ከካቢኔው ሚኒስትር ራሼሎ ኦማሞ ጋር በመገናገኘት ያላቸውን ስትራቴጂክ ግንኙነት የሚያጠናክሩ ሲሆን የኮቪድ-19 ወረርሽኝን በጋራ ለመዋጋት በሚያስችሉ መንገዶችም ዙሪያ እንደሚነጋገሩ ተመልክቷል፡፡

(በቪኦኤ ዘጋቢ ኒክ ቻንግ ከተዘጋጀው ዘገባ የተወሰደ)

XS
SM
MD
LG