በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩክሬን ቀዳማዊት እመቤት የዋሽንግተን ጉብኝት ውጤት እያሳየ መሆኑ ተገለጠ


የዩክሬን ቀዳማዊት እመቤት ኦሌና ዘለንስኪ
የዩክሬን ቀዳማዊት እመቤት ኦሌና ዘለንስኪ

የዩክሬን ቀዳማዊት እመቤት ኦሌና ዘለንስኪ በዩናይትድ ስቴትስ ያደረጉት ጉብኝት ውጤት ማሳየት እየጀመረ ነው ሲሉ ፕሬዚዳንት ቮሎዶሚር ዜለንስኪ ተናገሩ።

ፕሬዚዳንቱ በትናንት ምሽት ዕለታዊ መግለጫቸው "የዩናይትድ ስቴትስ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ሴኔተሮች ጄምስ ሪች፣ ሪቻርድ ብሉሚንቶል፣ ሮብ ፖርትማን፣ ቤንጃሚን ካርዲን፥ ሮጀር ዊከር፣ ጂን ሻሂን እና ሊንዚ ግራም ሩሲያ ዩክሬን ላይ የምታካሂደውን ጥቃት በዘር ማጥፋት ድርጊትነት የሚፈርጅ ውሳኔ በማርቀቅ ላይ ናቸው" ብለዋል።

በሌላ በኩል የዩክሬኑ ፕሬዚዳንት ከጦር አዛዦቻቸው ጋር ባደረጉት ውይይት "ኃይሎቻችንን ወደግንባሩ ስናዘምት ወራሪውን ድል ልንመታ እንደምንችል ተማምነናል" ብለዋል።

ሆኖም የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር "ከዶንባስ ክፍለ ግዛት አልፈን ጥቃት ልናካሂድ በመዘጋጀት ላይ ነን" ብለው ባስጠነቀቁ ማግስት ትናንት የሩስያ ኃይሎች የዩክሬንን ከተሞች በረጅም ርቀት የጦር መሳሪያ ደብድበዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዩናይትድ ስቴትስ አራት ተጨማሪ ሮኬት ተኳሽ መሳሪያዎች እና መድፎችን ለዩክሬን እንደምትልክ ረቡዕ ዕለት አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG