በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአውሮፓ ኅብረት በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ እንዲጣል ሃሳብ አቀረበ


የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሰላ ቮንደር ላይን
የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሰላ ቮንደር ላይን

በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ እንዲጣል የአውሮፓ ኅብረት ሃሳብ አቅርቧል፡፡

ጥሪው የቀረበው የሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን (ኔቶ) አገራት የመከላከያ ሚኒስትሮች ብራስልስ ውስጥ ተሰባስበው ለዩክሬን ተጨማሪ የመሣሪያ እገዛ በሚደረግበት ጉዳይ ላይ እየመከሩ ባለበት ወቅት ነው፡፡

ማዕቀቡ የኢንዱስትሪና የቴክኖሎጂ ውጤቶች ወደ ሩሲያ እንዳይላኩ በማድረግ ሩሲያ ለጦር መሣሪያ ሥርዓቷ የሚያስፈልጋትን ቴክኖሎጂ እንዳታገኝ የሚያደርግ ነው ሲሉ የአውሮፓ ኮሚሽን ፕሬዚዳንት ኡርሰላ ቮንደር ላይን ተናግረዋል፡፡ የማዕቀብ ሃሳቡ በተጨማሪም የኢራን አብዮታዊ ዘብ ሻሂድ ድሮኖችን ለሩሲያ እንዳይልክ የሚከለክል ነው፡፡

ሩሲያ ከኢራን በሚቀርብላት ድሮን የዩክሬንን መሠረተ ልማቶች አውድማለች የሚል ክስ ይቀርብባታል፡፡

ሌላው የማዕቀቡ ክፍል ደግሞ የሩሲያ የፕሮፖጋንዳ መሪዎችንና ወታደራዊ አዝዦችን ኢላማ ያደረገ ነው፡፡

ቮንደር ላይን እንደሚሉት ሩሲያ የፕሮፖጋንዳና የሃሰት ወሬ አሰራጮችን በመጠቀም የዓለምን ማኅበረሰብ ለማጋጨት መርዛማ የፈጠራ ወሬዎችን በመንዛት ላይ ነች፡፡

የኔቶ ዋና ጸሃፊ የንስ ስቶልተንበርግ በበኩላቸው በስብሰባው ላይ ሲናገሩ እንዳሉት ዩክሬን ሩሲያን መመከት እንድትችል ተጨማሪ የጦር መሣሪያ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋትና፣ አገራት ታንክና ሌሎች ከባድ መሣሪያዎችን ለመለገስ የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ጠይቀዋል፡፡

XS
SM
MD
LG