በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ የዩክሬን ኦዴሳ ከተማ ላይ የሚሳይል ጥቃት አደረሰች


ሩሲያ የዩክሬኗ ኦዴሳ ከተማ ባደረሰችው የሚሳይል ጥቃት የተጎዳ ህንፃ
ሩሲያ የዩክሬኗ ኦዴሳ ከተማ ባደረሰችው የሚሳይል ጥቃት የተጎዳ ህንፃ

ሩሲያ ዛሬ አርብ ማለዳ የዩክሬኗ ኦዴሳ ከተማ ባደረሰችው የሚሳይል ጥቃት ቢያንስ አስራ ሰባት ሰዎች መግደሏ ተዘግቧል። ብዙ ሰዎች እንደቆሰሉም ታውቋል። ከተተኮሱት ሚሳይሎች መካከል ቢያንስ አንዱ ኢላማ ያደረገው የሲቪሎች መኖሪያ አካባቢን መሆኑ ነው የተገለጸው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ የዩክሬን ባለሥልጣን እንደተናገሩት ከበርካታ ወራት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ትናንት ሀሙስ ከቤርዲያንስክ ወደብ 7000 ቶን እህል የጫነ መርከብ ተንቀሳቅሷል። እህሉ "ወደ ወዳጅ ሀገሮች የሚሄድ ነው" ብለዋል ባለሥልጣኑ።

በሌላ በኩል የወቅቱን የቡድን ሃያ ፕሬዚዳንትነቱን ከያዘችው ከኢንዶኒዥያ ፕሬዚዳንት ጆኮ ዊዶዶ ጋር ትናንት ሞስኮ ላይ የጋራ ጋዜጣዊ ጉባኤ ያደረጉት የሩስያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ዩክሬን ወደቦቿ ላይ የተቀበሩ ፈንጂዎችን የምታነሳ ከሆነ ከዩክሬን እህል ጭነው ለሚወጡ መርከቦች ደህንነት ዋስትና እንሰጣለን ብለዋል። ዩክሬን ወደቦቼን በሚቀበር ፈንጂ ያጠርኩት የሩስያን ጥቃት ለመከላከል በማለት ፈንጂውን ማጽዳት ላይ ስታመነታ ቆይታለች።

በሰሜን አትላንቲክ ቃል ኪዳን ድርጅት የመሪዎች ጉባኤ ላይ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደንን ጨምሮ ምዕራባውያን መሪዎች ለዩክሬን ወታደራዊ እና ሰብዓዊ ዕርዳታ መስጠታቸውን እንደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።

XS
SM
MD
LG