ኒው ዮርክ —
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ኢቲ 302 ባጋጠመው አደጋ ምክንያት ስለደረሰው የሕይወት መጥፋት በጥልቅ ማዘናቸውን የተባበሩት መንግሥት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ አስታወቁ።
የመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞችን ጨምሮ በአደጋው ምክንያት የሚወድዷቸውን ላጡ ቤተሰቦችና ሌሎችም ሁሉ፤ ለኢትዮጵያም ሕዝብና መንግሥት ባጠቃላይ ኀዘናቸውን ገልፀዋል ዋና ፀሐፊ ጉቴሬዥ።
በአደጋው የሞቱትን የድርጅቱን ሠራተኞች ዝርዝር ሁጌታ ለማወቅም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከኢትየጵያ ባለሥልጣናት ጋር እየሠራ መሆኑንም ዋና ፀሐፊው ማመልከታቸውን ቃል አቀባያቸው ስቴፈኒ ዱያሪችን ጠቅሳ ሪፖርተራችን ማርጋሬት በሽር ከኒው ዮርክ የመንግሥታቱ ድርጅት ጠቅላይ ፅሕፈት ቤት ዘግባለች።
የፌስቡክ አስተያየት መስጫ