በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተመድ የጸጥታ ም/ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ መከረ


የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አርማ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት አርማ

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ትናንት በኢትዮጵያ ትግራይ ክልልና በሃገሪቱ ሰሜናዊ አካባቢዎች ባለው የፀጥታና ሰብዓዊ ሁኔታዎች ላይ መክሯል።

የምክር ቤቱ ስብሰባ በአመዛኙ ያተኮረው በሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦቶች ላይ ይሁን እንጂ እየተዋጉ ያሉ ሁሉም ወገኖች በአስቸኳይ ግጭቶችን እንዲያቆሙና ወደ ድርድር እንዲገቡ ጠይቀዋል።

በተጨማሪም “የኤርትራ ሠራዊት ከኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉና በአፋጣኝ እንዲወጣ፣ ህወሓትም ከያዛቸው የአማራ እና የአፋር ክልሎች ተዋጊዎቹን እንዲያስወጣ፣ የአማራ ልዩ ኃይሎችና ሚሊሽያም ከምዕራብ ትግራይ አካባቢዎች እንዲወጡ” ሲሉ የምክር ቤቱ አባል ሃገሮች አምባሳደሮች አሳስበዋል።

የኢትዮጵያ መንግሥትም የእርዳታ አቅርቦት በሚሳለጥበት ሁኔታ ላይ አጠንክሮ እንዲሠራና መሰናክሎችን እንዲያስወግድ ጠይቀዋል።

በሙሉው ስብሰባ ላይ የተሳተፉት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዥ በመክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር “በጦርነት ጨርሶ መፍትሄ አይመጣም” ሲሉ ያሳሰቡ ሲሆን ይህን ሃሳባቸውንም የምክር ቤቱ አባላት ተጋርተውታል።

አባላቱ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንደሚደግፉም በየተራ ባደረጉት ንግግር አመክልተው ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ኢትዮጵያ መር የሆነና በአፍሪካ በሚደገፍ የድርድርና የዕርቅ ጥረትን እንደሚያበረታቱ አስታውቀዋል።

በስብሰባው ላይ የተገኙት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ታየ አፅቀሥላሴ መንግሥታቸው ሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦትን ለማሳለጥ እያደረገ ያለውን ጥረት እና ህወሕት ከዚህ ጦርነት ጋር በተያያዘና በሃገሪቱ ላይም አድርሷል ያሉትን ጥፋት ዘርዝረዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡

የተመድ የጸጥታ ም/ቤት በሰሜን ኢትዮጵያ ሁኔታ ላይ መከረ
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:12 0:00


XS
SM
MD
LG