በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ከሚወስኑ የአሜሪካ ግዛቶች አንዱ የሆነው ዊስከንሰን


የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ከሚወስኑ የአሜሪካ ግዛቶች አንዱ የሆነው ዊስከንሰን
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:21 0:00

የፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ውጤት ከሚወስኑ የአሜሪካ ግዛቶች አንዱ የሆነው ዊስከንሰን

በዩናይትድ ስቴትስ መካከለኛው ምዕራብ የሚገኘው በወተት ከብቶች እርባታ እና በቢራ ምርት የሚታወቀው ዊስከንሰን በመጪው ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወሳኝ ፍልሚያ የሚካሄድበት ግዛት ሆኖ ብቅ ብሏል።

እጅግ በጣም ተቀራራቢ የምርጫ ፉክክሮችን በማስተናገድ የሚታወቀው የዊስከንሰን ግዛት አስር የመራጭ ተወካዮች የሚሰጡት ድምፅም ቀጣዩ ፕሬዝዳንት ማን ሊሆን እንደሚችል ሊወስን ይችላል።

ግዛቱ የከተማም የገጠርም መራጮችን አሰባስቦ መያዙ ልዩ የሚያደርገው ሲሆን ከኢኮኖሚ እስከ ፅንስ ማቋረጥ መብቶች የሚያራምዷቸው አመለካከቶች የሀገሪቱን የፖለቲካ ክፍፍል የሚያንፀባርቅ ተደርጎም ይቆጠራል።

ግዛቱ አሸናፊውን የመወሰን አቅም እንዳለው የተረዱት ሁለቱ አውራ ፓርቲዎችም በዊስከንሰን ከፍተኛ መዋዕለ ነዋይ እያፈሰሱ ነው።

እጩዎቹ በዚህ በፖለቲካ ወዴት እንደሚያጋድል ለመረዳት አስቸጋሪ በሆነ ግዛት፣ በትልቁ ከተማ ሚልዋኪ እና በትንንሾቹ ከተማዎች እየተዘዋወሩ ባሉበት በዚህ ወቅት ታዲያ፣ የዊስከንሰን መራጮች እራሳቸውን የአሜሪካ ዲሞክራሲያዊ ሂደት እምብርት ሆነው አግኝተውታል። የአሜሪካ ድምጿ ቫኒሳ ጆንስተን ዘገባ ዝርዝሩን ይዟል፡፡

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG