በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰሜን ኢትዮጵያ ሁኔታ እየተባባሰ ነው - ተመድ


ፎቶ ፋይል፦ በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ፀሃዬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የምግብ ልገሳ ለመቀበል ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።
ፎቶ ፋይል፦ በትግራይ ክልል ሽሬ ከተማ ፀሃዬ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በግጭት የተፈናቀሉ ሰዎች ጊዜያዊ መጠለያ ውስጥ የምግብ ልገሳ ለመቀበል ወረፋ በመጠባበቅ ላይ ናቸው።

በሰሜን ኢትዮጵያ በተለይ ትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ሰብዓዊ ሁኔታ እየተባባሰ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ የኢትዮጵያ ተጠባባቂ አስተባባሪ ግራንት ሊየቲ ትናንት በሰጡት መግለጫ ትግራይ የነበረው የእርዳታ ምግብ ክምችት ባለፈው ነሐሴ 14/2013 ዓ.ም ማለቁን አመልክተዋል።

“ለችግሩ መፈጠር ምክንያት የሆነው ሰብዓዊ አቅርቦቶችን ለማሳለፍ የሚወስደው ረጅም ጊዜ ነው” የሚሉት ሊየቲ የኢትዮጵያ መንግሥት ያልተገደበ ተደራሽነትን እንዲፈቅድ ጠይቀዋል።

ለችግሩ ህወሓትን ተጠያቂ የሚያደርገው የኢትዮጵያ መንግሥት ወቀሳውን አይቀበልም።

ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያድምጡ፡፡

የሰሜን ኢትዮጵያ ሁኔታ እየተባባሰ ነው - ተመድ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:44 0:00


XS
SM
MD
LG