በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 ኮንጎ ውስጥ ያልታወቀ በሽታ 50 ሰዎችን ገደለ


የዓለም ጤና ድርጅት፣ ዋና መሥሪያ ቤት፤ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ
የዓለም ጤና ድርጅት፣ ዋና መሥሪያ ቤት፤ ስዊዘርላንድ ጄኔቫ

ሰሜን ምዕራብ ኮንጎ ውስጥ የተከሰተ ያልታወቀ ወረርሽኝ ከ50 በላይ ሰዎችን መግደሉን ከሥፍራው የሚገኙ ሃኪሞች እና የዓለም ጤና ድርጅት ባለሥልጣናት በትላንትናው ዕለት አስታውቀዋል።

የመጀመሪያው የበሽታው ምልክቶች በሚታዩበት እና ለሕመሙ የታጋለጠ ሰው ለሕልፈት በሚዳረግበት መካከል ያለው ጊዜ በአማካይ የ48 ሰዓታት ዕድሜ ብቻ መሆኑን ጠቅሰው፣ “በእጅጉ አሳሳቢ ያደረገውም ይህ ሁኔታ ነው” ሲሉ የክልሉ የወረርሽኞች መከታተያ ማእከል የሆነው የቢኮሮ ሆስፒታል የሕክምና ድሬክተር ሰርጅ ንጋሌባቶ ወረርሽኙን አስመልክቶ ለአሶሺየትድ ፕሬስ በሰጡት አስተያየት አስረድተዋል ።

ባለፈው ጥር 23 ቀን 2017 ዓም የተቀሰቀሰው ወረርሽኝ ለሕልፈት የተዳረጉትን 53 ሰዎች ጨምሮ እስካሁን 419 ሰዎች ለበሽታው መጋለጣቸው ተዘግቧል። የዓለሙ ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቢሮ አክሎ እንዳመለከተው የበሽታው መከሰት የታወቀው የመጀመሪያዎቹ የወረርሽኙ ሰለባ የሆኑ ሶስት ህጻናት፣ የሌሊት ወፍ ሥጋ ከተመገቡ እና በ48 ሰዓታት ዕድሜ ከፍተኛ ትኩሳትና የደም የመፍሰስ አደጋ የሚያስከትሉ በሽታዎች ምልክቶችን አሳይተው ለሕልፈት ከተዳረጉ በኋላ ነው።

የዱር እንስሳት በሥፋት ለምግብነት በሚውሉባቸው አካባቢዎች ከእንስሳት ወደ ሰው የሚዛመቱ በሽታዎች ለረጅም ጊዜ ሲያሳስቡ ቆይተዋል። የዚህን መሰል ወረርሽኞች አሃዝ ባለፉት አስርት ዓመታት ብቻ በአፍሪቃ ውስጥ ከ60 በመቶ በላይ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት እንደ አውሮፓውያን የዘመን አቆጣጠር በ2022 አስታውቆ ነበር።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG