በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ምሁራን ልዩነትን ከሚያሰፉ ትርክቶች ይልቅ ለሰላም ግንባታ እንዲሠሩ ተጠየቀ


ምሁራን ልዩነትን ከሚያሰፉ ትርክቶች ይልቅ ለሰላም ግንባታ እንዲሠሩ ተጠየቀ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:35 0:00

ምሁራን ልዩነትን ከሚያሰፉ ትርክቶች ይልቅ ለሰላም ግንባታ እንዲሠሩ ተጠየቀ

በሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት ወቅት ምሁራን ሰላማዊ መፍትሔን የማፈላለግ ድርሻቸውን እንዳልተወጡ የገለጹ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች አመራሮች፣ በግጭቱ የተፈጠሩ ክፍተቶችን ለመሙላትና ኅብረተሰቡን መልሶ ለማገናኘት እየሠሩ እንደኾነ ተናገሩ።

ለአሜሪካ ድምፅ የተናገሩ አንድ ተንታኝ፣ በጦርነቱ ወቅት የሰላም መፍትሔን መጠቆም ሲገባቸው፣ የችግሩ አካል ኾነው የቆዩ አንዳንድ ዩኒቨርሲቲዎች እና ምሁራን እንደነበሩ ጠቁመዋል፡፡ አሁን ግን “ያን መካስ ይኖርባቸዋል፤” ሲሉ አክለዋል።

የሰላም ሚኒስቴር በበኩሉ፣ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለሰላም ግንባታ ግንባር ቀደም ኾነው ይሠሩ ዘንድ እንደሚያበረታታ ገልጿል።

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ “የሰላም ግንባታ በኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል፣ ባለፈው ቅዳሜ እና እሑድ ባዘጋጀው ዓለም አቀፍ ኮንፈረስ፣ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ክልሎች የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ኃላፊዎች እና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተዋል።

ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG