በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ተዋጊ ጄቶች በሶሪያ ከኢራን ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ መደቦችን ደበደቡ


በደቡብ ሶሪያ የሚገኘው የአሜሪካ ወታደራዊ ሠፈር (ፎቶ ፋይል - ኤፒ)
በደቡብ ሶሪያ የሚገኘው የአሜሪካ ወታደራዊ ሠፈር (ፎቶ ፋይል - ኤፒ)

ከኢራኑ አብዮታዊ ዘብ ጦር ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ እና በምሥራቅ ሶሪያ የሚገኙ ሁለት መደቦችን የአሜሪካ ተዋጊ ጄቶች ዛሬ ዓርብ መደብደባቸውን ፔንታጎን አስታውቋል።

ድብደባው፤ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በቀጠናው በሚገኙ የአሜሪካ ወታደራዊ ይዞታዎችና የአሜሪካ መከላከያ አባላት ላይ በድሮን እና በሚሳዬል ለተፈጸመው ጥቃት መልስ መሆኑን ፔንታጎን አስታውቋል።

ቡካማል በተባለ ስፍራ አቅራቢያ በሁለት ኤፍ-16 ተዋጊ ጄቶች በተፈጸመው ድብደባ፣ ከኢራኑ አብዮታዊ ዘብ ጦር ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ የጦር መሣሪያዎች እና ማከማቻዎች መመታታቸውን ፔንታጎን አስታውቋል። ሥፍራው የኢራኑ አብዮታዊ ዘብ ጦር በአሜሪካውያኑ ላይ ጥቃት ለመፈጸም የዋሉት መሣሪያዎችን ለማከማቸት ይጠቀምበት እንደነበር ፔንታጎን ጨምሮ አስታውቋል።

ወደፊት ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይኖር በኢራን የሚደገፉ ቡድኖች ላይ ጠንካራ ምት እንደሚሰነዘር፣ ሆኖም ግን በቀጠናው ግጭት እንዳይስፋፋ ጥንቃቄ እንደሚወሰድ ፔንታጎን አስታውቋል።

ዛሬ በተፈጸመው ድብደባ በሰውም ሆነ በንብረት ላይ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ አልታወቀም ተብሏል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG