በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

 
የኤርትራው አሰብ ወደብ የተባበሩት አረብ ኤማረቶች ባህር ሃይሎች እንደታዩበት ተገለጸ

የኤርትራው አሰብ ወደብ የተባበሩት አረብ ኤማረቶች ባህር ሃይሎች እንደታዩበት ተገለጸ


አሰብ ወደብ
አሰብ ወደብ

ከአገልግሎት ውጭ ሆኖ የቆየው የኤርትራው አሰብ ወደብ የተባበረው የአረብ ኤማሬቶች የባህር ሃይል መርከቦች እንደታዩበት የስለላ ምንጮች ሲገልጹ ቆይተዋል።

ኢንተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ የተባለው በአለም ደረጃ ስለሚከሰቱት ቀውሶች የሚከታተለው ቡድን የአፍሪቃ ቀንድ ክፍል በለሙያ ሰዲክ ባርነስ ኤርትራ አሰብ ወደብን በአምስት መቶ ሚልዮን ዶላር ለተባበሩት የአረብ ኤማሬቶች አከራይታለች ተብሎ እንደሚታመን ገልጸዋል። የተባበረው የአረብ ኤሚሬቶች የአሰብ ወደብን በማከራየት ለየመን ተደራሽነት ያገኛል ኤርትራ ደግሞ ያጠረባትን ገንዘብ ታገኛለች።

የኤርትራ መንግስት ድምጹን አጥፍቶ የአሰብ ወደብን በ $500 ሚልዮን ዶላር ሳይሆን አይቀርም ተብሎ በሚታመን ገንዘብ እንዳከራየ ሰዲክ ባርነስ ገልጸዋል።

በአለም ደረጃ ስለሚከሰቱት ቀውሶች የሚከታተለው ቡድን
በአለም ደረጃ ስለሚከሰቱት ቀውሶች የሚከታተለው ቡድን

“የተባበረው የአረብ ኤሚሬቶች የአሰብ ወደብን የባህር ሀይል ሰፈር ለማድረግ ተከርይቷል። የባህር ሀይሉ ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በሳውዲ አረብያ መሪነት በየመን ይካሄድ በቆየው የአየር ድብደባ ዘመቻ የሚያገለግል ሳይሆን አቀርም።”

ባርነስ አያይዘውም የተባበረው አረብ ኤማረቶች የአሰብ ወደብን የተከራየው በዝቅተኛ ዋጋ መሆኑን ሲገልጹ ጉዳዩ ጽምጽ አጥፍቶ የተከናወነ ባይሆንና በይፋ ተደርጎ ቢሆን ኖሮ ከዛ የበዛ ዋጋ ባስከፈለ ነበር ይላሉ።

የአረብ ኤማሬቶች ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በጂቡቲ ያካሄዱት የነበረውን እንቅስቃሴ ስላጡ በሱማሊላንድ ያለው የበርበራ ወደብን እንደአማራጭ ወስደዋል ብለዋል ባርነስ።

ኤርትራ አሰብ ወደብን በማከራየት በምታገኘው ገንዘብ እንደምትጠቀም ሰዲክ ባርነስ አውስተዋል።

በመሰረቱ የአውሮፓ ህብረት በአሁኑ ወቅት ለኤርትራ ገንዘብ የሰጠው ከሁለት አመታት በፊት ባለበት ቆሞ የነበረውን የህብረቱ የልማት እቅድን ለማንቀሳቀስ እንደሆነ ባርንስ ጠቁመዋል። አብዛኛው ገንዘብ የመብራት ሃይል አቅርቦትን በማዳበር ላይ እንዲውል ይጠበቃል።

የልማት እንቅስቃሴው ኤርትራውያን ከሀገራቸው እንዳይወጡ ሊያነሳሳቸው ይችላል ሲባል ደግሞ ውሎ አደሮ ገደብ የሌለው የሃገራዊ አገልግሎትን ያቆማል የሚል ነበር። ነገር ግን ይህ የሚሆን አይመስልም ሲሉ ባርንስ አስገንዝበዋል።

ኤርትራ በሀገሪቱ ከሚካሄደው የማእድን ስራም ገቢ ታገናለች ስለሚባለው ጉዳይ ደግሞ ባርነስ ገቢ አላት ግን የተጋነን ነው ብለዋል።

“ከማእድን ገቢ አላቸው ግን እንደታሰበው አይመስለኝም። እኔ እስከማውቀው ድረስ ኤርትራውያኑ ለማዕደን ኩባንያዎቹ አስቀድመው ከሚገባው በላይ የሆነ ተስፋ ሰጥተዋል። መዋለ ነዋይ ለማፍሰስ ሲሉ ብዙ ገንዘብ ተበድረዋል። የማእድኑ ሥራ በአክስዮን የሚሰራ በመሆኑ ብዙም ንጹህ ትርፍ እያገኙ አይደለም።”

ኤርትራ ከመገለል እየወጣች ነውን? ለሚለው ጥያቄ በአለም ደረጃ ስለሚከሰቱት ቀውሶች የሚከታተለው ቡድን የአፍሪቃ ቀንድ ክፍል ባለሙያ ሰዲክ ባርነስ ሲመልሱ፣ ኤርትራ በበኩልዋ ተግለየ አላውቅም፣ ከመላው አለም ጋር ጥሩ ግንኑነት አለኝ ባይ ናት። ይህ እንዳለ ሆኖ ግን ኤ

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የኤርትራው አሰብ ወደብ የተባበሩት አረብ ኤማረቶች ባህር ሃይሎች እንደታዩበት ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:10 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG