በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ አየር መንገድ አውሮፕላን በድንገት እንዲያርፍ ተደረገ


የአሜሪካው ዩናይትድ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 787
የአሜሪካው ዩናይትድ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 787

የአሜሪካው ዩናይትድ አየር መንገድ ንብረት የሆነ አውሮፕላን፣ ረቡዕ ዕለት ከበሩ ጋር ተያይዞ በደረሰ ማስጠንቀቂያ ምክንያት በድንገት ፍሎሪዳ ግዛት ታምፓ ከተማ ላይ ድንገት ማረፉን የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ አስታወቁ።

አውሮፕላኑ "ያጋጠመው ችግር ከተፈታ በኋላ" በድጋሚ እንዲበር መደረጉንም አየር መንገዱ ሐሙስ ዕለት አስታውቋል።

አደጋው ያጋጠመው ኤይርባስ ኤ319 የተሰኘው አውሮፕላን ሲሆን፣ ባለፈው ሳምንት የአላስካ አየር መንገድ ንብረት የሆነ ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን፣ ከኦሪገን ግዛት ተነስቶ በበረራ ላይ ሳለ መስኮቱ መገንጠሉ ይታወሳል።

በዩናይትድ አውሮፕላን ላይ የተፈጠረውን ችግር ለማወቅ የተደረገውን ምርመራ ተክትሎ ይፋ የተደረገው የመነሻ ሪፖርት፣ የአውሮፕላኑ በር ላይ የሚገኝ አመልካች መብራት በመብራቱ አውሮፕላኑ አቅጣጫውን ቀይሮ እንዲያርፍ መደረጉን፣ የታምፓ አየር ማረፊያ ቃል አቀባይ አስታውቀዋል። የእሳት አደጋ ሰራተኞችም አውሮፕላኑ ሲያርፍ በተጠንቀቅ ቆመው ሲጠባበቁ ነበር።

የዩናይትድ አየር መንገድ ቃል አቀባይ በበኩላቸው፣ ፍሎሪዳ ከሚገኘው ሳራሶታ ከተማ ተነስቶ ወደ ቺካጎ ይበር የነበረው አውሮፕላን ታምፓ ላይ እንዲያርፍ የተደረገው ለጥንቃቄ መሆኑን ገልፀው፣ አውሮፕላኑ በሰላም ማረፉንና ችግሩ ከተስተካከለ በኋላ በረራውን እንዲቀጥል መደረጉን አመልክተዋል።

በአውሮፕላኑ ላይ 123 ተሳፋሪዎች እና አምስት ሰራተኞች እንደነበሩም ተገልጿል።

መድረክ / ፎረም

XS
SM
MD
LG