በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የምዕራብ ዳርፉር አገረ-ገዥ መገደላቸውን ተመድ አወገዘ


ዳርፉር፣ ሱዳን
ዳርፉር፣ ሱዳን

በትናንትናው ዕለት በምዕራብ ዳርፉር አገረ ገዢ ካሚስ አብደላ አባክር ላይ የተፈጸመው ግድያ እጅግ እንዳስደነገጠው እና እንደሚያወግዘው በሱዳን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሽግግር ድጋፍ ሰጪ ተልዕኮ አስታውቋል።

ለግድያው የአረብ ሚሊሻዎች እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ተጠያቂ እንደሆኑ አስተማማኝ የዓይን ምስክሮች ቃል ሰጥተዋል”

“ለግድያው የአረብ ሚሊሻዎች እና የፈጥኖ ደራሽ ኃይሉ ተጠያቂ እንደሆኑ አስተማማኝ የዓይን ምስክሮች ቃል ሰጥተዋል” ሲል የመንግሥታቱ ድርጅት ተልዕኮ መግለጫ አስታውቋል። የፈጥኖ ደራሹ ኃይሉ ክሱን አስተባብሏል።

የመንግሥታቱ ድርጅት የሱዳን ድጋፍ ሰጪ ተልዕኮው በተጨመሪም ድርጊቱን የፈጸሙት በአስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ፣ ሁከቱም የበለጠ እንዳይስፋፋ ጠይቆ የሱዳን ሕዝብ በጥላቻ ንግግር እና በጎሳ ልዩነት ተጠልፎ ግጭት ውስጥ እንዳይወድቅ ብልህነት የተሞላው መፍትሄ እንዲሻ ልዑኩ ተማጽኖ አቅርቧል።

በቀጠናው በአደራዳሪነት ትልቅ ሚና የነበራቸውና የጁባን የሰላም ስምምነት ከፈረሙት አንዱ የነበሩት የአገረ ገዢው መገደል በእጅጉ የሚያሳዝን መሆኑን መግለጫው አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG