በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም ጎስቋላ ሕፃናት


መንግሥታት ከተሞችን ሲገነቡና አገልግሎቶችን ሲያሻሽሉ ማዕከላዊው ትኩረት ሕፃናት መሆን እንደሚገባቸው ዩኒሴፍ አሣሰበ፡፡

የተባበሩት መንግሥታት የሕፃናት አጣዳፊ ድጋፍ ድርጅት - ዩኒሴፍ በትልልቅና በትናንሽ ከተሞች የሚኖሩ በብዙ መቶ ሚልዮኖች የሚቆጠሩ ልጆች መሠረታዊ የሆኑትን የጤና፣ የትምህርት፣ የንፁህ ውኃና የንፅህና ጥበቃ አገልግሎቶች እንደማያገኙ ገልጿል።

ዩኒሴፍ በያዝነው ዓመት የዓለም ሕፃናት ስለሚገኙበት ሁኔታ ያወጣው ሪፖርት በከተሞች ውስጥ በሚገኙ የደኸዩ ሠፈሮች ውስጥ የሚኖሩ ልጆች ያሉበትን አስከፊ ሁኔታ ያሣያል።

እነዚህ ሕፃናት ከዓለም እጅግ የበዛውን ያጡና ለብዙም ጉዳቶች የተጋለጡ መሆናቸውን ዩኒሴፍ ይናገራል፡፡

አመፃና ሁከት በበረከተባቸው አካባቢዎች ነው የሚኖሩት፡፡ የሚካሄድባቸው ብዝበባ እጅግ የከበደ ነው፡፡ መሠረታዊ ናቸው የሚባሉ አገልግሎቶች ተነፍገዋቸዋል፡፡

ታግለው፣ ተፍጨርጭረውም ማሸነፍ የሚችሉባቸው ዕድሎች ሁሉ ጠብበውባቸዋል፡፡

ዝርዝሩን ከሊሣ ሽላይን የጄኔቫ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG