በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አፋር ክልል የተፈናቃዮች መገደል እንዳሳሰበው ዩኒሴፍ ገለፀ


በኢትዮጵያ አፋር ክልል ከሁለት መቶ የሚበልጡ ተፈናቃዮች ተገድለዋል ተብሎ የወጡ ሪፖርቶች በጥልቅ አሳስበውናል ሲል ዩኒሴፍ አስታወቀ።

የተባበሩት መንግሥታት የህጻናት መርጃ ድርጅት/ዩኒሴፍ/ ዛሬ ባወጣው መግለጫ ባለፈው ሃሙስ አፋር ክልል ውስጥ ተፈናቃይ ቤተሰቦች በተጠለሉባቸው አንድ ጤና ጣቢያ እና አንድ ትምህርት ቤት ላይ በተፈጸመ ጥቃት ከአንድ መቶ የሚበልጡ ልጆች ያሉባቸው ከሁለት መቶ የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸውን ያመለከቱት ሪፖርቶች እጅግ ያሳሰበው መሆኑን አስታውቋል።

ትግራይ ውስጥ ለወራት ከተካሄደው ውጊያ ተከትሎ ከመካከላቸው ቢያንስ አንድ መቶ ስድሣ ልጆችን ጨምሮ አራት መቶ ሽህ ሰዎች በጽኑ ረሃብ ሁኔታ ውስጥ እንዳሉ ያመለከተው ዩኒሴፍ ባሁኑ ወቅት በትግራይ እና በአዋሳኝ የአማራ እና የአፋር ክልሎች አራት ሚሊዮን ሰዎች በአጣዳፊ የምግብ ዕጦት ውስጥ እንደሚገኙ አውስቷል።

እስካሁን በግጭቶች ምክንያት ቀያቸውን ለቀው በወጡት ሁለት ሚሊዮን ሰዎች ላይ ባለፉት ቅርብ ጊዚያት በተካሂዱት ውጊያዎች አንድ መቶ ሽህ አዲስ ተፈናቃዮች የተጨመሩ መሆኑን ዩኒሴፍ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG